avatar
EthioTube
@ethiotube
25.03.2026 02:37
ታዋቂው የሙዚቃ አቀናባሪ ካሙዙ ካሳ በዘንድሮ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲን በመወከል እንደሚወዳደር ታወቀ

ታዋቂው የሙዚቃ አቀናባሪ ካሙዙ ካሳ በዘንድሮ ዓመት በሚካሔደው ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ እንደሚሳተፍ ታውቋል። ካሙዙ የካ ክፍለከተማን በመወከል ለአዲስ አበባ ምክር ቤት እንደሚወዳደር ተገልጿል። ገዢውን ብልጽግና ፓርቲ የተቀላቀለው ካሙዙ፤ በማኀበራዊ ገጹ በሚያስተላልፋቸው መልዕክቶች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን በማድነቅ እና በማወደስ ይታወቃል።

በተመሳሳይ ሁኔታ ከዚሁ ክፍለከተማ ብልጽግና ፓርቲን በመወከል ለአዲስ አበባ ምክር ቤት በእጩነት የቀረበችው ጋዜጠኛ በሻቱቶለማሪያም ናት። ጋዜጠኛ በሻቱ በኢቢሲ መዝናኛ ቻናል የመዝናኛ ፕሮግራሞችን በመምራት ረዘም ላለ ጊዜ አገልግላለች። በተጨማሪ በአፋን ኦሮሞ የተሰሩ የኪነጥበብ ውጤቶችን በማወዳደር ሽልማት የሚያበረክተውን የኦዳ ሽልማት መሥራች መሆኗም ይታወቃል።

#Ethiopia #KamuzuKassa #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa #EthiopianPolitics #EthiopianMusic #ProsperityParty
2 8 2.3K

Обсуждение 2

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram