avatar
EthioTube
@ethiotube
24.03.2026 00:50
“የደህንነት ሰዎች ክትትል እያደረጉብኝ ነው” የኢሕአፓ ፀሓፊ ሚስጥረሥላሴ ታምራት

ክትትል አድራጊዎቹ “እስከ ግድያ ድረስ የሚያስቡ[ናቸው]”

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ(ኢሕአፓ) እና የትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ ዋና ፀሓፊ የሆነችው ሚስጥረሥላሴ ታምራት በመንግሥት የደህንነት ኃይሎች ክትትል እየተደረገባት መሆኑን ተናግራለች። ክትትል አድራጊዎቹ “እስከ ግድያ ድረስ የሚያስቡ” መሆናቸውንም አስታውቃለች።

ሚስጥረ ሥላሴ ርዕዮት ከተሰኘ የበይነ መረብ ሚዲያ ጋር ባደረገችው ቃለመጠይቅ፤ በዚህ ዓመት በሚደረገው የምርጫ ሒደት ውስጥ በመሳተፋቸው ከመንግሥት ከፍተኛ ጫና እየደረሰባቸው እንደሆኑ አስረድታለች። በተለይ የግል እንቅስቃሴዋ በደህንነት ሰዎችክትትል ውስጥ መውደቁን ተናግራለች። በዚህ ክትትል ምክንያት “ከሰዎች ጋር እንደልብ ለመገናኘት አለመቻሏን” አስረድታለች።

“ከሰዎች ጋር በነፃነት መገናኘት አትችልም። ሁሉም ቦታ ታያቸዋለህ፤ ሁሉም ቦታ አሉ። የመንግሥት አካላት ናቸው እናውቃለን። ደግሞ እንድናውቅም ያደርጉናል። እንደሚከታተሉን እንደሚያዩን፣ከእነሱ እይታ እንደማናመልጥ፣ ምንም እያደረግንም ቢሆን” ስትል በደህንነት ሰዎች ስለሚደረገባት ክትትል ገልፃለች።

ሚስጥረ ሥላሴ በሰጠችው ማብራሪያ የደህነነት ሰዎች “በቢሮ አካባቢ፣በሆቴሎች ውስጥ፣ቤት አካባቢ” እንደሚንቀሳቀሱ ማወቅ እንደቻለችም ተናግራለች። ከክትትሉ በተጨማሪ “ሕይወታቸውን ላይ አደጋ እስከማድረስ የሚችል እቅድ ስለመኖሩ መስማቷንም” በነበራት ቆይታ ተናግራለች።

“አንዳንድ ሰዎች አሉ [ከመንግሥት] ውስጥም በኩል የምንሰማቸው መረጃዎች አሉ።

#Ethiopia #AddisAbaba #MistresilasieTamerat #EPRP #EthioTube #Africa
2 1 2.3K

Обсуждение 2

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram