avatar
EthioTube
@ethiotube
22.03.2026 20:59
ኢራን የዘጋችውን የሆርሙዝ ባሕር ወሽመጥ በሁለት ቀናት ውስጥ ካልከፈተች የኃይል ማምጫዎቿ ይወድማሉ ስትል አሜሪካ አስጠነቀቅች

ኢራን የዘጋችውን የሆርሙዝ ባሕር ወሽመጥ በሁለት ቀናት ውስጥ ካልከፈተች የኃይል ማምጫዎቿን እንደሚያወድሙት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዝተዋል። አሜሪካ እና እስራዔል በጋራ ኢራን ላይ ጥቃት ከፈጸሙ በኋላ የተቀሰቀሰው በቀጠናው የተቀሰቀሰው ጦርነት አራተኛ ስምንቱን ይዟል።

ኢራን ከወሰደቻቸው እርምጃዎች ውስጥ አንዱ በርካታ መርከቦች የሚተላለፉበትን የሆርሙዝ ባሕር ወሽመጥ መዝጋት አንዱ ነው። ይህ የባሕር ወሽመጥ መዘጋቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ ነዳጅ ወደ ሀገራቸው የሚያስገቡ ሀገራትን ጫና ውስጥ ከትቷል። የዓለም 20 በመቶ ነዳጅ የሚተላለፍበት ይህ የባሕር መስመር በመዘጋቱ ዜጎች ነዳጅ ቆጥበው እንዲጠቀሙ ኢትዮጵያ ጥሪ አቅርባለች።

ትራምፕ በመልዕክታቸው ኢራን የሆርሙዝ ባሕር ወሽመጥን በ 48 ሰዓታት ውስጥ “ያለምንም ማስፈራሪያ ሙሉ በሙሉ ካልከፈተች የተለያዩ የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎቿን እንደመስሳለን” ማለታቸውን አልጀዚራ ዘግቧል። ቴህራን ለትራምፕ ዛቻ በሰጠችው ምላሽ፤ ጥቃት የሚሰነዘርባት ከሆነ በቀጠናው የሚገኙ የአሜሪካ የኃይል መሠረተ ልማቶች ላይ ተመሳሳይ እርምጃ እወስዳለሁ ስትል ተናግራለች።

የኢራን ሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በርካታ አገሮች መርከቦቻቸው በሰላም እንዲያልፉ ጥያቄ እያቀረቡ መሆኑን ገልጾ፤ የሆርሙዝ ወሽመጥ ከአሜሪካና ከአጋሮቿ በስተቀር ለሁሉም ክፍት ነው ማለቱን ዘገባው አመላክቷል።

#USA #Iran #Israel #UnitedStates #WorldNews #AmharicNews #EthioTube #MiddleEast
1 1 1.8K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram