avatar
EthioTube
@ethiotube
22.03.2026 17:18
በደቡብ ጎንደር ዞን አምስት ባለሥልጣናት በታጣቂዎች መገደላቸው ተነገረ

በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን ታጣቂዎች በሰነዘሩት ጥቃት የወረዳ ዋና አስተዳዳሪዎችን ጨምሮ ቢያንስ አምስት የአካባቢው ባለሥልጣናት እንደተገደሉ ተሰምቷል። ከደቡብ ጎንደር ዞን ኮሙኒኬሽን በጉዳዩ ላይ ባወጣው መግለጫ በመንግሥት የሥራ ኃላፊዎቹ ላይ ግድያው የተፈፀመው መጋቢት 09/2018 ዓ.ም. “ነፍጥ አንግበው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች” ነው በማለት ወንጅሏል።

በክልሉ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል እየተካሔደ የሚገኘው ግጭት መፍትሔ ሳያገኝ ሦስት ዓመት ሆኖታል። የደቡብ ጎንደር ዞን በመግለጫው “የጥፋት ኃይሎች” ሲል የጠራቸው ታጣቂዎች በነፋስ መውጫ እና ሐሙሲት ከተማ ላይ ግጭት በመፍጠር በሥራ ላይ ያሉትን የላይ ጋይንት፣ የወገዳ፣ የነፋስ መውጫ፣ የደራ እና ሐሙሲት ከተማ የነበሩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና የፀጥታ መዋቅር ላይ ያነጣጠረ የጥፋት ጥቃት መፈጸማቸውን አስታውቋል።

በጥቃቱ “ጀግኖቻችን ለባንዳና ተላላኪ እጅ አንሰጥም፤ ሕዝባቸውንም ጥለን አንሸሽም በማለት የአፄ ቴወድሮስን ፅዋ ተቀብለዋል” ሲል የባለሥልጣናቱን ሞት ገልጿል። ከተገደሉት ኃላፊዎች ውስጥ የደራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እስቲበል ጓዴ፣ የደራ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፈንታሁን ድረስ እንዲሁም የወረዳው የፖሊስ አዛዥ፣የስማዳ ወረዳ አስተዳዳሪ እና የሐሙሲት ከተማ ከንቲባ እንደሚገኙበት ተዘግቧል።

ካለፈው ወር አንስቶ የመከላከያ ሠራዊት በዞኑ የሚገኙ አካባቢዎችን ለቅቆ በመጣቱ በአካባቢው የነበሩት የፀጥታ ኃይሎች የክልሉ አድማ በታኝ፣ ፖሊስ እና ሚሊሻ መሆናቸው ተሰምቷል።

#Gondar #Amhara #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa #EthioTube
1 1 1.8K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram