avatar
EthioTube
@ethiotube
20.03.2026 16:41
የፌደራል መንግሥት ትግራይ ክልል ላይ “ያደረገውን የበጀት ክልከላ የሚቃወም” ሰላማዊ ሰልፍ ሊደረግ ነው

የፌደራል መንግሥት ትግራይ ክልል ላይ “ያደረገውን የበጀት ክልከላ የሚቃወም” ሰላማዊ ሰልፍ በሚቀጥለው ሳምንት ይደረጋል ተብሏል። መጋቢት 15/2018 ዓ.ም. በትግራይ ክልል የሚካሔደውን ሰላማዊ ሰልፍ የክልሉ ትምሕርት ቢሮ፣ የትግራይ ክልል መምኀራን ማኅበር እና የተማሪ ወላጆች ማኀበር በጋራ ያዘጋጁት መሆኑን ኢትዮ ቲዩብ ሰምቷል።

በዚህ ጉዳይ ላይ መግለጫ የሰጡት የክልሉ ትምሕርት ቢሮ ኃላፊ ኪሮስ ግዑሽ (ዶ/ር) ከሰላም ስምምነቱ በኋላ በክልሉ የሚገኙ መምሕራን እስካሁን ድረስ 16 ወራት ውዝፍ ደመወዝ አልተከፈላቸውም ብለዋል። ይህ ክፍያ ሳይፈፀም የፌደራል መንግሥት “በጀት በመከልከሉ” መምሕራን ያለፈው የየካቲት ወር ደመዝ ሳይከፈላቸው መቅረቱን አብራርተዋል።

በሀገሪቱ ግጭት ውስጥ ባሉ ሌሎች ክልሎች የመምሕራን ደመዝ አልተከለከለም ያሉት የትምሕርት ቢሮ ኃላፊው፤“ትግራይ ላይ የተደረገው መድሎ የታየበት ነው” ሲሉ ውቅሰዋል። “በበጀት ክልከላው” ሳቢያ በክልሉ የተለያዩ ወረዳዎች የትምሕርት ሒደቱ እየተቋረጠ ነው መባሉንም ሰምተናል።

የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አማኑኤል አሰፋ ከዚህ ቀደም በሰጡት ማብራሪያ ትግራይ ክልል በየወሩ በጀት እንደሚላክላት አስታውሰው ከጥቅምት ወር በኋላ ግን መቋረጡን ተናግረዋል።

“በየወሩ 2.3 ቢሊዮን ብር አካባቢ ማግኘት አለበት ክልሉ። [ግን] ከጥቅምት እስከ የካቲት ወር 2.4 ቢሊዮን ብር ብቻ ነው ያገኘው” ብለዋል። በተጨማሪ ነዳጅ ወደ ክልሉ “ሙሉ በሙሉ መግባት አቁሟል፤ አንድም ነገር የለም” ሲሉ የፌደራል መንግሥት እየፈጸመ ያለውን ክልከላ አስረድተዋል።

#Ethiopia #Tigray #TadesseWorede #EthioTube
1 1.9K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram