avatar
EthioTube
@ethiotube
18.03.2026 19:54
በአንድ ወር ውስጥ ብቻ 1750 ባለትዳሮች ፍቺ ፈፅመዋል ተባለ

በአዲስ አበባ ከተማ በአንድ ወር ውስጥ ብቻ 1750 ባለትዳሮች ፍቺ መፈፀማቸው ተሰምቷል።

በከተማዋ ባለፉት ስድስት ወራት ከተከናወኑ
19, 800 ጋብቻዎች በአጠቃላይ ከ5,800 በላይ ፍቺዎች መመዝገባቸውን የከተማዋ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታውቋል።

የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጥጋቡ ሹመይ ለኤ ኤም ኤን ዲጂታል በሰጡት ማብራሪያ፤ ከተመዘገቡት ፍቺዎች መካከል 1,750 ያህሉ ፍቺ በተፈጸመ በ30 ቀናት ውስጥ መሆኑን ገልፀዋል።ቀሪዎቹ 695 ፍቺዎች ደግሞ ዘግይተው የተመዘገቡ መሆናቸውን አብራርተዋል።

ከትዳር ፍቺ በስተጀርባ ስላሉ ምክንያቶች ማብራሪያ የሰጡት የሕግና ማኅበራዊ ጉዳይ አማካሪ ወ/ሪት መቅደስ አስፋው፤ በትዳር ውስጥ የሚፈጠሩ ችግሮች ድንገተኛ ሳይሆኑ፣ ይስተካከላሉ በሚል ቸልተኝነት ትኩረት ሳይሰጣቸው የታለፉ ጉዳዮች ውጤት መሆናቸውን ዘገባው አመላክቷል።

#Ethiopia #AddisAbaba #EthiopianCouples #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
7 1.7K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram