avatar
EthioTube
@ethiotube
16.03.2026 20:46
ቭላድሚር ፑቲን በጋሞ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገለፁ

የሩሲያው ፕሬዝዳንት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን በተከሰተው የመሬት መንሸራተት በዜጎች ላይ ያጋጠመን ጉዳት አስመልክቶ ሃዘናቸውን ገልጸዋል። ፕሬዝዳንቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በነበራቸው የስልክ ውይይት ላይ ነው ሀዘናቸውን የገለጹት።

በአዲስ አበባ የሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ፤ መሪዎቹ በፖለቲ፣ በንግድ፣ በኢኮኖሚ እና በሰብዓዊ ዘርፎች ባሉ በወቅታዊ የሁለትዮሽ ትብብር ላይ መነጋገራቸውን አስታውቋል። ፕሬዝዳንት ፑቲን “በሀገሪቱ ደቡባዊ ክፍል በደረሰው የመሬት መንሸራተት አሳዛኝ አደጋ ምክንያት ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶኛል” በማለት መልዕክታቸውን ለዐቢይ አሕመድ ማስተላለፋቸውን ኤምባሲው በመግለጫ አመላክቷል።

በጋሞ ዞን 4 ወረዳዎች በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የ 81 ሰዎች አስክሬን ተገኝቶ ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈፅሟል። ሆኖም እስካሁን ድረስ 125 ሰዎች መግኘት እንዳልቻሉ ከዞኑ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች የተገኘው መረጃ ያመላክታል። ይህን አደጋ አስመልክቶ ሀዘናቸው የገለጹት የሩሲያው ፕሬዝዳንት “ለተጎጂ ቤተሰቦች ልባዊ መፅናናትንና እመኛለሁ” ብለዋል። በተፈጥሮ አደጋው የአካል ጉዳት ላጋጠማቸው ዜጎች ሁሉ በቶሎ እንዲያገግሙ ምኞታቸውን በስልክ ውይይቱ ላይ ማንሳታቸው ተገልጿል።

#Ethiopia #Russia #VladimirPutin #Gamo #GamoZone #Mudslide #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
1 2.1K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram