avatar
EthioTube
@ethiotube
16.03.2026 20:25
“ነዳጅን በቁጠባ ተጠቀሙ” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

“በቅርቡ በተጠና ሁኔታ የነዳጅ ቁጠባ እርምጃዎች ለኀብረተሰቡ ይገለፃል” የገንዘብ ሚኒስቴር

በመካከለኛው ምሥራቅ በተፈጠረው ቀውስ የተነሣ ነዳጅ ገዝተው የሚጠቀሙ ሀገሮች “እንደልብ ለማግኘት መቸገራቸውን” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገልጸዋል። ይህ “ችግር ተፈትቶ ወደ መደበኛው የነዳጅ አቅርቦት ሥርዓት እስክንመለስ ድረስ ነዳጅን በቁጠባና ለመሠረታዊ ነገሮች ቅድሚያ በመስጠት መጠቀም ይኖርብናል” ሲሉ በማኅበራዊ ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል።

አሜሪካ እና እስራኤል በጋራ ኢራን ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ የመካከለኛው ምሥራቅ ቀጠና ላለፉት ሁለት ሳምንታት በጦርነት ውስጥ ይገኛል። በዚህ ምክንያት ኢራን የዓለም 20 በመቶ ነዳጅ የሚተላለፍበት የሆርሙዝ ወሽመጥ በመዝጋቷ የነዳጅ ግብይት ጫና ውስጥ ገብቷል። በተጨማሪም ዋጋው ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል።

በባለፈው ሳምንት በዚህ ጉዳይ ላይ መግለጫ የሰጡት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ በሀገሪቱ የነዳጅ አቅርቦትን አስተማማኝ ለማድረግ “በሌሎች አማራጮች አፋጣኝ የነዳጅ ግዢ እየተደረገ ነው” ማለታቸው ይታወሳል።

ሚኒስትሩ አክለውም የኢትዮጵያ መንግሥት በዓለም አቀፍ ደረጃ የተፈጠረውን የነዳጅ አቅርቦትና የዋጋ ቀውስ ተከትሎ ሊመጣ የሚችለውን ጫና ለመቋቋም “በተወሰነ ደረጃ ከዴፖዎቻችን ለኀብረተሰቡ ማቅረቡን” አስታውቀዋል። በተጨማሪ “አጣዳፊ ግዢዎችን በማድረግ አስተማማኝ አቅርቦት እንዲቀጥል እያደረገ ይገኛል” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዛሬው መልዕክታቸው “ነዳጅን በቁጠባና ለመሠረታዊ ነገሮች ቅድሚያ በመስጠት መጠቀም ይኖርብናል” ብለዋል።

#Ethiopia #AddisAbaba #AbiyAhmed #PMAbiy #EthiopianNews #EthioTube #Africa
1 2 1.2K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram