avatar
EthioTube
@ethiotube
15.03.2026 19:49
የትራንስፖርት ዋጋ ላይ እስከ 20 ብር የሚደርስ ዋጋ ጭማሪ ተደረገ

በወቅታዊ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ የተደረገውን የዋጋ ማስተካከያ ተከትሎ የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ እስከ 20 ብር የሚደርስ ጭማሪ ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል። ዛሬ ይፋ በተደረገው ጭማሪ የከተማ አውቶብስ አገልግሎትን ጨምሮ በሚኒባስ፣ በሚዲባስና የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎችን የሚመለከት ነው ተብሏል።

ከነገ ጀምሮ ተፈፃሚ በሚሆነው አዲሱ የሚኒባስ ትራንስፖርት ዋጋ ከዚህ በፊት ከነበረው ታሪፍ ላይ እስከ 10 ብር እንዲጨምር ሆኗል። 25 ብር የነበረው የጉዞ ዋጋ ወደ 35 ብር ከፍ ብሏል። 7.6 እስከ 20 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍነው የ 45 ብር የጉዞ ዋጋ ወደ 55 ብር ከፍ ብሏል። 30 ብር የነበረው የጉዞ ታሪፍ ከነገ ጀምሮ 40 ብር እንዲሆን ተወስኗል። 15 ብር ይከፈልበት የነበረው ታሪፍ አሁን ላይ ወደ 20 ብር ተደርጓል። በሚኒባስ ተሽከርካሪ ከሁለት እስከ አምስት ኪሎሜትር የሚሸፍነው ጉዞ ከ 15 ብር ወደ 20 ብር ከፍ ብሏል።

የሃይገር እና ቅጥቅጥ የትራንስፖርት አገልግሎት ላይም በተመሳሳይ ሁኔታ ቀድሞ ከነበረው ዋጋ ላይ ከ 5 እስከ 10 ብር የሚደርስ ጭማሪ ተደርጓል። ዛሬ ይፋ የተደረገው የትራንስፖርት ታሪፍ ከፍተኛውን ጭማሪ ያደረገው የባስ ትራንስፖርት ላይ ነው። ከአርባ እስከ ሃምሳ ኪሎሜትር የሚሸፍነው የታሪፍ ዋጋ ከ 50 ብር ወደ 70 ብር ከፍ እንዲል ተደርጓል። 40 ብር የነበረው የጉዞ ታሪፍ 20 ብር ጨምሮ 60 ብር ገብቷል።

#Ethiopia #AddisAbaba #PublicTransportation #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
2 1.7K

Обсуждение 2

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram