avatar
EthioTube
@ethiotube
11.03.2026 21:07
በጋሞ ዞን በተከሰተው የመሬት ናዳ የ52 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ 50 ሰዎች ደግሞ እስካሁን አለመገኘቱ ተገለፀ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ ማዞ ዶይሳ ቀበሌ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ 52 ሰዎች ሲሞቱ ተጨማሪ 50
ሰዎች ደግሞ ደብዛቸው እንደጠፋ ተሰምቷል።
በዞኑ የመሬት ናዳው የተከሰተው ትላንት ማክሰኞ መጋቢት 1/ 2018 ዓ.ም. በጣለ ከባድ ዝናብ መሆኑ ተገልጿል።

የደረሱበት ያልታወቁ 50 ሰዎችን የመፈለግ ሥራ በከፍተኛ ርብርብ እየተከናወነ እንደሚገኝ የዞኑ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዛሬ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ከዚህ ቀደም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተለያዩ ዞኖች በተደጋጋሚ የመሬት ናዳ አደጋ ሲከሰትበት እንደነበር ይታወሳል።

ሐምሌ 15/ 2016 ዓ.ም. በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት ከ250 በላይ ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል። በተመሳሳይ ሁኔታ በባለፈው ዓመት
በወላይታ ዞን በተከሰተ አደጋ የሰዎች ሕይወት አልፏል።

በጋሞ ዞን ትላንት በተከሰተው አደጋ ደብዛቸው የጠፉትን 50 ሰዎች የማፈላለግ ጥረት መቀጠሉ ተመላክቷል።

#Ethiopia #Gamo #GamoZone #Mudslide #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
1.7K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram