avatar
EthioTube
@ethiotube
11.03.2026 00:28
“የአሰብን ወደብ ኢትዮጵያ ካልተጠቀመችው ይበሰብሳል እንጂ ምንም ሊሆን አይችልም” ሜ/ጀነራል ተሾመ ገመቹ

የአሰብን ወደብ “በኤርትራ ያሉ ግመሎች እንኳን አያገኙትም”

አሰብ የሚባለው ወደብ ሲሰራ ወይም ዲዛይን ሲሆን ኢትዮጵያን ብቻ እንዲያገለግል ታስቦ ነው ሲሉ የመከላከያ የውጭ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ተሾመ ገመቹ ተናግረዋል። ጄነራሉ አክለውም ወደቡን ኢትዮጵያ ካልተጠቀመችበት “ይበሰብሳል እንጂ ምንም ሊሆን አይችልም” ማለታቸውን ሰምተናል።

ሜ/ጄነራል ተሾመ ገመቹ ይህን የተናገሩት የባህር በር እና ወደብን አስመልክቶ በአድዋ ሙዚየም ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ ነው። ሰላሳ ደቂቃ ገደማ በሚሆነው ማብራሪያቸው ኢትዮጵያ “እንኳን በሰጥቶ መቀበል ሕግ በነፃ የባሕር በር ይገባት ነበር” ብለዋል።
ለዚህ ንግግራቸው ሞሮኮ ለጎረቤት ሀገራት በነፃ የባሕር በር መስጠቷን በምሳሌነት አንስተዋል። “ሞሮኮ ምዕራብ ሰሃራ አካባቢ ላሉ ሀገሮች፣ ጎረቤታቸው ላሉ ሀገሮች በነፃ የባሕር በር ሰጥታለች። ይሄን ለመድረክ ፍጆታ ሳይሆን እዚህ ሞሮኮ ኤምባሲ መጠየቅ ትችላላችሁ። ምንም ሳያስከፍሉ በነፃ። ይሄ ታሪክ ሳይሆን አሁን በሥራ ላይ ያለ ነገር ነው። የኛ ጉዳይ የምቀኝነት ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር እንደ ሞሮኮ ዓይነት ልብ ስለሌላቸው ካልሆነ በስቀር እንኳን በሰጥቶ መቀበል ሕግ ነፃም ይገባን ነበር ነው” በማለት ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የባሕር በር ቢኖራት ተጠቃሚዎቹ “አሁን ባሕር በር አይገባችሁም የሚሉት የጎረቤቶቻችን ቡድኖች እና ግለሰቦች ናቸው” ብለዋል። ጄነራሉ በማብራሪያቸው የአሰብን ወደብ በመጥቀስ ለኤርትራ ሳይሆን ኢትዮጵያን ብቻ እንዲያገለግል ታስቦ የተሰራ ነው ብለዋል።

#Ethiopia #Eritrea #Assab #EthioTube #Africa
2 2 1.8K

Обсуждение 2

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram