avatar
EthioTube
@ethiotube
08.03.2026 20:27
በደቡብ ወሎ በመኀል ሳይንት ወረዳ 5 የቤተ ክርስቲያን  አገልጋዮች መገደላቸው ተሰማ

"26 ኦርቶዶክሳውያን ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ታውቋል"

በደቡብ ወሎ  በመኀል ሳይንት ወረዳ በምትገኘው ርዕሰ አድባራት ወታዕካ ነገሥት አትሮንሰ ማርያም ገዳም ላይ ተተኩሷል በተባለ ከባድ መሳሪያ 3 ዲያቆናትና አንዲት አቃቢ መገደላቸውን የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ጥቃቱ የተፈፀመው ትላንት ቅዳሜ የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ነው። በዚሁ ዕለት ሥርዓተ ቅዳሴው እንደተጠናቀቀ "ከደቂቃዎች በኋላ የዕለቱን ቅዳሴ የመሩ  መነኮሳትና ዲያቆናት ወደ ደጀ  ሰላም ሲያመሩ   በተተኮሰው  ከባድ  መሣሪያ" ተገድለዋል ተብሏል።

በተጨማሪም በዕለቱ በገዳሟ ቅጥር ጊቢ የነበሩ 26 ምዕመን ላይ ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ዘገባው አመላክቷል።

ከሞቱት አገልጋዮች መካከል ሦስቱ በዛሬው ዕለት ቀብራቸው በገዳሙ ተፈፅሟል። ሁለቱ አስክሬን ደግሞ ወደ ቤተሰባቸው ተሸኝቷል ተብሏል።

በአካባቢው በተደጋጋሚ በተፈፀመው የከባድ መሣሪያ ድብደባ በገዳሙ የነበሩ ከ60 በላይ የአብነት ተማሪዎችና ከሞት የተረፉት አገልጋዮች አካባቢውን ለቀው መሸሻቸው ተነግሯል።

ሆኖም ዘገባው ከባድ መሳሪያውን ወደ ገዳሟ የተኮሰውን አካል በይፋ አልገለፀም።

#Ethiopia #Wollo #SouthWollo #EOTC #EthiopianOrthodox #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
1 1 2.1K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram