avatar
EthioTube
@ethiotube
08.03.2026 11:07
የጎንደር ከተማ ኢማም የሆኑት ሸይኽ ሐጂ ሙሃመድ ዘይኑ መገደላቸው ተገለፀ

የጎንደር ከተማ ኢማም ነሆኑት ሸይኽ ሐጂ ሙሃመድ ዘይኑ መገደላቸውን የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አስታውቋል።

እኒህ የሐይማኖት አባት ከመስጂድ ወጥተው ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲመለሱ ከተማ መሃል በደረሰባቸው ጥቃት ሕይወታቸው እንዳለፈ ተገልጿል።

ምክር ቤቱ፤ "ሸይኹ ላይ ለተፈፀመው አስነዋሪ ተግባር ሕዝባችን ላይ ለሚደርሰው በደል ፍትህ እንፈልጋለን" ሲል ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።

"መንግስት በንፁሃን ላይ እየደረሰ ያለውን አስነዋሪ ተግባር በየትኛውም ሰው በሆነ የሰው ልጆች ሁሉ የሚደርስን የሰዋዊ መገለጫ ያልሆኑ ተግባራትን ሊያስቆምና ግዴታ የሆነውን ጥበቃ ና ከለላ ሊያደርግ ይገባል" በማለት ምክርቤቱ በመግለጫው አሳስቧል።

ሸይኽ ሐጂ ሙሃመድ ዘይኑ ላይ ጥቃት ስላደረሱት አካለት በመግለጫው በይፋ ባይጠቀሰም በታጣቂዎች በጉዳዩ ላይ የወጡ መረጃዎች ግን በተተኮሰባቸው ጥይት እንደተገደሉ ያትታል።

#Ethiopia #Gondar #Amhara #EthiopianMuslims #HajiMohammedZeinu #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
1 1.7K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram