avatar
EthioTube
@ethiotube
06.03.2026 20:29
የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ሴቶችን “አስገድዶ እንደሚደፍር” እና “ለወሲብ ባርነት” እየዳረጋቸው መሆኑ በምርመራ ሪፖርት ተጋለጠ

“ታጣቂ ቡድኑ የፈጸማቸው ጥፋቶች የጦር ወንጀል ሊባሉ የሚችሉ ናቸው”

በአሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሰው ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት እያለ የሚጠራው ቡድን ሴቶችን “አስገድዶ እንደሚደፍር” እና “ለወሲብ ባርነት” እየዳረጋቸው መሆኑን አምነስቲ ኢንተርናሽናል በምርመራው አጋልጧል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት የተፈረጀው ታጣቂ ቡድኑ “በጅምላ ግድያ”፣ “የዜጎችን ንብረት በማውደም”፣ “ከቤት ንብረት በማፈናቀል” ንጹኃን ነዋሪዎች ላይ መጠነ ሰፊ ጉዳት እንደሚያድርስም ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች በሪፖርቱ አመላክቷል።

ተቋሙ ዛሬ የካቲት 27/2018 ዓ.ም. ያወጣው 28 ገፅ ሪፖርት፤ ታጣቂ ቡድኑ በስፋት በሚንቀሳቀስባቸው በቄለም ወለጋ ዞን በሚገኙ ሳዮ እና አንፊሎ በተሰኙ ወረዳዎች ላይ የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን የሚያትት ነው። መንግሥት ኦነግ ሸኔ የሚለውና ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት እያለ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን ላለፉት ሰባት ዓመታት መጠነ ሰፊ የመብት ጥሰት ሲፈጽም እንደነበር ተገልጿል። አምነስቲ ለምርመራ ሪፖርቱ ዝግጅት በቡድን የመደፈር ጥቃት የደረሰባቸውን 10 ተጎጂዎችን አነጋግሯል። ከእነዚህም መካከል ሰባቱ ጥቃቱ በደረሰባቸው ወቅት ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ነበር። አምስቱ ሴቶች ደግሞ “ለወሲብ ባርነት ተዳርገው” እንደነበር ተመላክቷል። ቃላቸውን ከሰጡት ተጎጂዎች ውስጥ አንዷ ሴት የመደፈር ጥቃት የደረሰባት በመከላከያ ሰራዊት አባላት እና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ታጣቂዎች መሆኑን ገልጻለች።

#Ethiopia #Oromia #OLA
3 2 1.9K

Обсуждение 3

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram