avatar
EthioTube
@ethiotube
04.03.2026 10:09
“በጭራሽ ትግራይ ላይ የሚጀመር ጦርነት እንደሌለ ላረጋግጥ እወዳለሁ” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

“ሻዕቢያ ዳግም ሕዝባችንን እንዲበድል እድል አንሰጥም ምናልባት ከሞከረ ደግሞ የመጨረሻ ሙከራው ነው የሚሆነው ብዬ ነው እኔ የማምነው "

የፌደራል መንግሥት በርካታ ሰራዊቱን ወደ ትግራይ በማጓጓዝ ክልሉን እንደከበበ እየተነገረ ቢሆንም፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ግን “በጭራሽ ትግራይ ላይ የሚጀመር ጦርነት እንደሌለ ላረጋግጥና ለመግለጽ እወዳለሁ” ሲሉ አስታውቀዋል። ነገር ግን ህወሓት ከቃላት አልፎ ወደ ትንኮሳ ከገባ ውጊያ እንደማይቀር አመልክተዋል።

ጠቅላይሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት በትግረኛ ቋንቋ በሰጡት ቃለመጠይቅ ነው። በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ትላንት ምሽት በተላለፈው ቆይታቸው ትግራይን እና የኤርትራን የተመለከተ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ዐቢይ በማብራሪያቸው ህወሓትን “ከ 50 ዓመት በፊት በነበረ እሳቤ ተቸንክሮ የቆየ” ቡድን ነው በማለት ተችተዋል።

ከሁለት ዓመት በላይ የተካሔደውን ጦርነት የቋጨውን የፕሪቶሪያው ስምምነት እንዳይፈጸም ምክንያት የሆነውም ህወሓት ነው ሲሉ ከስሰዋል። ስምምነቱን “ራሱ ከሕግ አፈንግጦ ለዳግም ጦርነት እንደምክንያት እያቀረበው ነው” በማለት ገልጸዋል። ዐቢይ አክለውም ህወሓት በሰፊው ወታደራዊ ዝግጅት ላይ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

የፌደራል መንግሥት የልማት በጀት እየላከ ቢሆንም ህወሓት ግን በጀቱን “ለታጣቂዎች ቀለብ እያዋለው ነው” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ምንም እንኳን ቡድኑ ይህን ቢያደርግም በትግራይ ላይ ጦርነት የመክፈት ፍላጎት የለንም ማለታቸው ተሰምቷል። ሆኖም ወታደራዊ ትንኮሳ ካዳረገ ግን ከዚህ ቀደም ከነበረው በተለየ ሁኔታ ውጊያ ሊኖር እንደሚችል አመልክተዋል።

#Ethiopia #AbiyAhmed #Tigray #Eritrea
1 3 2.4K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram