avatar
EthioTube
@ethiotube
02.03.2026 21:05
“የኢትዮጵያ መንግሥት ፋኖን እንድናጠፋ ጥሪ አቅርቦልን ነበር” አቶ አማኑኤል አሰፋ የህወሓት ም/ሊቀመንበር

“ትግራይን የጦርነት አውድማ ለማድረግ ፈቃደኞች ስላልሆንን የመከላከያ ኃይል ወደ ክልሉ እንዲገባ አንፈቅድም”

የኢትዮጵያ መንግሥት ከፋኖ ጋር “ወደቁርሾ ሲገባ አጋጣሚውን ተጠቅመን ፋኖን እንድናጠፋ፣ የጦርነቱ አካል እንድንሆን በተለያየ ጊዜ ጥሪ ቀርቦልን” ነበር ሲሉ የህወሓት ም/ሊቀመንበር እና የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ም/ፕሬዝዳናት የሆኑት አቶ አማኑኤል አሰፋ ተናገሩ።

አቶ አማኑኤል የትግራይን ክልል ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ በሰጡት ቃለመጠይቅ፤ የፌደራል መንግሥት ወደ ጦርነት ለመግባት ጫፍ ላይ ደርሷል በማለት ገልጸዋል። ለዚህ ገለፃቸው በማስረጃነት ያነሱት የፌደራል መንግሥት ክልሉን፤ በአፋር፣በወሎ፣በምዕራብ ትግራይ በኩል መክበቡን ነው። በትግራይ በኩል ግን የጦርነት ፍላጎትም ሆነ ዝግጅት አለመኖሩን ተናግረው የፕሪቶሪያ ስምምነት እንዲፈጸም ነው የምንፈልገው ብለዋል።

የፌደራል መንግሥት በትግራይ ውስጥ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት በዋናነት በፕሪቶሪያ ውስጥ ያሉ ግዴታዎችን ፈጽሞ ትግራይ ከጦርነቱ በፊት ወደነበረችበት ክልላዊ ቁመና መመለስ አለበት ሲሉ አቶ አማኑኤል ተናግረዋል። ይሁን እንጂ መንግሥት ይሄን ግዴታውን ሳይፈጽም ሠራዊቱን ወደ ክልሉ ማስገባት አይችልም፤ ፈቃደኞች አይደለንም ብለዋል።

“የኢትዮጵያ መንግሥት ጄኖሳይድ ፈጽሟል። ያ ችግር ሳይፈታ መልክ ሳይዝ የኢትዮጵያ መንግስት ወደ ትግራይ የሚገባው እውነትም ትግራይ እንደ አንድ ክልል ችግሮቿ ተፈትቶ ከሌላ አካል ለመዋጋት ነው? ወይስ ሌላ ጄኖሳይድ ለመፈጸም ነው ወደ ትግራይ የሚመጣው? ምን ኢንሹራንስ አለ?” ሲሉ ጠይቀዋል።

#Ethiopia #Tigray #Fano #Amhara #EthioTube #Africa
1 2.4K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram