avatar
EthioTube
@ethiotube
28.02.2026 20:30
የመሬት ሊዝ ክፍያ በሚል እስከ 150 ሚሊዮን ብር የተጠየቁት የሸገር ከተማ ቤት አልሚዎች

“አዲሱ የሊዝ ተመን ከመደበኛው ክፍያ 6 ሺህ እጥፍ ጨምሯል”

በኦሮሚያ ክልል የሚገኘው የሸገር ከተማ አስተዳደር በሪልስቴት አልሚዎች፣በነዋሪዎች እና ሌሎች ባለንብረቶች ላይ ከፍተኛ የመሬት ሊዝ ክፍያ እየጠየቀ መሆኑ ተሰምቷል። በዚህ አሠራር እስከ 150 ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉ የተጠየቁ ግለሰቦች ጉዳዩን ለፌደራል መንግሥት ካሳወቁ በኋላ የሸገር ከተማ አስተዳደር “የእንደራደር ጥያቄ” እንዳቀረበላቸው መናገራቸውን ዘ ሪፖርተር አስነብቧል።

ከስድስት ዓመት በፊት የተመሠረተው ሸገር ሲቲ በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ የሚገኙ 6 የኦሮሚያ ክልል ከተማዎችን በመያዝ የተመሠረተ ነው። በርካታ ኢንዱስትሪዎች፣ የቤት አልሚዎች (የሪልስቴት ባለቤቶች) የሚገኙበት ሸገር ከተማ በነዋሪዎች ተደጋጋሚ ቅሬታ ሲቀርብበት ቆይቷል። ኢትዮ ቲዩብ ከዚህ ቀደም የተለያዩ ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ በሠራው ዘገባ፤ “ለሚሊሻ”፣“ለቀይ መስቀል”፣ “ለኢንሹራንስ”፣ “የስፖርታ ማዘውተሪያ ግንባታ” በሚሉ ምክንያቶች አስገዳጅ ክፍያ እንደሚሰበሰብ መዘገቡ አይዘነጋም።

አሁን ደግሞ የከተማው ነዋሪዎች እና የሪልስቴት ባለቤቶች “ወደኋላ ተመልሶ የሚታሰብ የሊዝ ክፍያ” መጠየቃቸውን ገልጸዋል። በዚህ ሳቢያ የተተመነባቸው ብር ከፍተኛ መሆን ዘገባው አመልክቷል። ከመደበኛው የሊዝ ተመን 6 ሺህ እጥፍ እንደጨመረ የተገለጸው የሊዝ ክፍያ የሕግ መሠረት የለውም ሲሉ ነዋሪዎች መናገራቸው ተመላክቷል። በለገጣፎ የሚገኝ ስሙ ያልተገለጸ ሪልስቴት ውስጥ የሕግ አማካሪ የሆኑ ግለሰብ ደንበኛቸው 150 ሚሊዮን ብር ተተምኖበት “በአስቸኳይ እንዲከፍል” በከተማው አስተዳደር መታዘዙን ተናግረዋል።

#Ethiopia #ShaggarCity #Oromia #EthioTube #Africa
4 2K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram