avatar
EthioTube
@ethiotube
28.02.2026 20:03
አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት መክፈታቸውን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎቹን ሰርዟል

ዛሬ ቅዳሜ የካቲት 21/2018 ዓ.ም. ጠዋት እስራኤል እና አሜሪካ በጋራ ኢራን ላይ በከፈቱት ጥቃት ምክንያት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ የሚያደርገውን በረራ መሰረዙን አሳውቋል። አየር መንገዱ በጉዳዩ ላይ ባወጣው አጭር መግለጫ በመካከለኛው ምስራቅ ባለው ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ምክንያት ወደ ቀጠናው የማደርጋቸውን የተወሰኑ በረራዎች ሰርዣለሁ ብሏል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራውን የሰረዘባቸው ከተማዎች ኦማን፣ ቴል አቪቭ፣ ዳማም እና ቤይሩት ናቸው። ዛሬ ማለዳ ኢራን ላይ በተሰነዘረው ጥቃት በዋና ከተማዋ ቴህራን ተደጋጋሚ የሚሳዔል ፍንዳታ ተከስቷል። ሚናብ በተባለች ከተማ በሚገኝ የሴቶች ትምሕርት ቤት በደረሰ ጥቃት ደግሞ 53 ተማሪዎች መገደላቸው አልጀዚራ ዘግቧል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይህን ጉዳይ በቅርበት እንደሚከታተል ገልጾ፤ የተሳፋሪዎቻችንን እና የሠራተኞቻችንን ደህንነት ለማረጋገጥ ተገቢውን እርምጃ ሁሉ እንወስዳለሁ ብሏል።

#Ethiopia #EthiopianAirlines #MiddleEast #UnitedStates #Israel #Iran #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
1 1.7K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram