avatar
EthioTube
@ethiotube
24.02.2026 21:24
መንግሥት የአዲስ ስታንዳርድ የበይነ-መረብ ሚዲያን አገደ

የኢትዮጵያ መንግሥት የአዲስ ስታንዳርድ የበየነ-መረብ መገናኛ ብዙኃንን አግዷል። የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ባወጣው መግለጫ የሚዲያው ምዝገባ ምስክር ወረቀት ከዛሬ የካቲት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ መሰረዙን አሳውቋል።

"አዲስ ስታንዳርድ የበየነ-መረብ መገናኛ ብዙኃን የሚዲያ ስነ ምግባርን፣ የኢትዮጵያ ሕጎች እና የሀገርንና የሕዝብን ብሔራዊ ጥቅም አደጋ ላይ የሚጥሉ ዘገባዎችን በተደጋጋሚ በማሰራጨት ላይ ይገኛል" ሲል ባለሥልጣኑ ወንጅሏል።

"ይህ አደገኛ ተግባር" በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ሬጉላቶሪ ስራዎች የተረጋገጠ እና በዜጎች በርካታ ጥቆማና ቅሬታ ሲቀርብበት የቆየ ነው ተብሏል።

በዚህ ምክንያት ባለሥልጣኑ ይህንኑ ድርጊት በመመርመር አዲስ ስታንዳርድ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን "እንዲታረም እና ከአጥፊ አካሄዱ እንዲቆጠብ በተደጋጋሚ ምክር ሲሰጥ ቢቆይም ለመታረም ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል" ማለቱን ተመልክተናል።

በዚህ ውሳኔ ምክንያት ከዛሬው እለት አንስቶም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የአዲስ ስታንዳርድ የበየነ-መረብ መገናኛ ብዙኃን የምዝገባ ምስክር ወረቀት እንደተሰረዘ እና ምንም አይነት የሚዲያ ፈቃድ እና እውቅና እንደሌለው ለሁሉም አካል ያሳውቃል ሲል ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

የኢትዮጵያ መንግስት በተመሳሳይ መልኩ የዋዜማ ራዲዮን እና ሮይተርስን ማገዱ ይታወሳል።

#Ethiopia #EthiopianPress #EthiopianMedia #EthiopianBroadcastingAuthority #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa #AddisStandard
1 2 2.4K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram