avatar
EthioTube
@ethiotube
23.02.2026 23:41
“ምርጫ ቦርድ ያስተላለፈውን ውሳኔ እናከብራለን” የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በአማራ እና ትግራይ ክልል መካከል አከራካሪ የሆኑ አካባቢዎች “የይገባኛል ጥያቄው እስከሚፈታ ድረስ” ከትግራይ ክልል ውጭ እንዲሆኑ ያስተላለፈውን ውሳኔ እናከብራለን ሲል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ገለጸ።

ፓርቲው ዛሬ ባደረገው የአስፈጻሚ ኮሚቴ አስቸኳይ ስብሰባ “ምርጫ ቦርድ ያስተላለፈውን ውሳኔ ከፕሪቶሪያ ስምምነት መንፈስ አንጻር እናከብረዋለን” ብሏል። ምንም እንኳን ፓርቲው ውሳኔን ቢቀበልም በአከራካሪ ቦታዎቹ ላይ የክልል ምክር ቤት ምርጫ አይካሔድም መባሉን እንደሚቃወም አመላክቷል። “ሕዝባችን ለክልሉ ምክር ቤት ጭምር የመምረጥ መብቱ ሊከበርለት ይገባል” ብሏል።
ፓርቲው አክሎም “ይህ ሂደት ዘላቂ መፍትሔ እስኪያገኝ ድረስ፣ ሕዝባችን በባህል፣ በሥነ-ልቦናና በማንነት ከሚመስለው ከአማራ ክልል ምክር ቤት ጋር የሚወከልበት ልዩ ፖለቲካዊ ውሳኔ እንዲተገበር እንጠይቃለን” ሲል በዛሬው መግለጫ አትቷል። መንግስት ከሀገራዊ ሁኔታዎች አንጻር የሚወስዳቸው ውሳኔዎች “ሙሉ በሙሉ የማይመቹን ናቸው” ያለው ፓርቲው የሕዝብን ጥያቄ ያለጊዜ ገደብ ማቆየት ለፖለቲካ ሽፍጥ በር ይከፍታል ሲል ስጋቱን ገልጿል።

ችግር ፈጣሪዎች የሚደመጡበት፣ የሕዝብ ድምጽ የሚታነቅበት ሁኔታ ከእንግዲህ እንዲቀጥል አንፈቅድም ሲል በመግለጫው አመላክቷል። “የሕዝባችን ጥያቄ የጥፋት ኃይሎችን ለማባበል ወይም ለሽንገላ ሊውል አይገባም” ሲል ፓርቲው አሳስቧል። ምንም እንኳን የአማራ ሕዝብ መሠረታዊ ጥያቄዎችና የሀገራችን ውስብስብ ችግሮች በምርጫ ብቻ እንደማይፈቱ ብንገነዘብም፤ አብን በግንቦት ወር በሚደረገው ሰባተኛው አጠቃላይ ምርጫ ለመሳተፍ የሚያስችለውን ስትራቴጂ ነድፎ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑንም ተናግሯል።

#Ethiopia
3 2.1K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram