avatar
EthioTube
@ethiotube
23.02.2026 20:29
በአማራ እና ትግራይ ክልል መካከል አከራካሪ የሆኑ አካባቢዎች “የይገባኛል ጥያቄው እስከሚፈታ ድረስ” ከትግራይ ክልል ውጭ እንዲሆኑ ተወሰነ

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ፤ በአማራ እና ትግራይ ክልል የይገባኛል ጥያቄ የሚነሳባቸው አካባቢዎች “የይገባኛል ጥያቄው እስከሚፈታ ድረስ” ከትግራይ ክልል ውጭ እንዲሆኑ በፌዴሬሽን ምክር ቤት መወሰኑን አስታውቋል። ቦርዱ ይህን የገለጸው ዛሬ የካቲት 16/2018 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ነው። ይህን መግለጫ ተከትሎ የትግራይ ክልል አስተዳደር እና የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

ምርጫ ቦርድ በ ጥር 25/2018 ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ደብዳቤ ተልኮለት እንደነበር ገልጿል። በዚህ ደብዳቤ ላይ በትግራይ እና አማራ ክልል መካከል አካራካሪ የቆዩ አምስት የምርጫ ክልሎች “የይገባኛል ጥያቄው እስከሚፈታ ድረስ ከትግራይ ክልል ውጭ ሆነው ለብቻቸው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ እንዲደረግ መወሰኑን” አመላክቷል።

ከትግራይ ክልል አስተዳደር ውጭ እንዲሆኑ የተወሰኑት ሁመራ፣አዲረመፅ፣ኮረም አፍላ፣የራያ እና አላማጣ የተሰኙት የምርጫ ክልሎች መሆናቸው ታውቋል። በነዚህ አካባቢዎች ለክልል ምክር ቤት የሚደረገው ምርጫ በዘንድሮ ዓመት እንደማይካሔም በመግለጫው ላይ ሰፍሯል። ምርጫ ቦርድ “የክልል ምክር ቤት ምርጫው በአካባቢዎቹ ላይ የተነሳው የይገባኛል ውዝግብ በሕገ መንግሥቱ ውሳኔ ሲፈታ አመቺ ጊዜ ተመርጦ ወደፊት እንዲካሔድ ተወስኗል” ብሏል። ይህን የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ ተከትሎ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የተቃውሞ መግለጫ አውጥቷል።

የዛሬው ውሳኔ ሕገ-መንግሥቱንና የፕሪቶሪያውን ስምምነት በግልጽ የሚጥስ ነው ብሏል።

#Ethiopia #Tigray #Amhara #NEBE #NEBEthiopia #TPLF #Simret #EthioTube #Africa
2 2K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram