avatar
EthioTube
@ethiotube
23.02.2026 00:06
ባንኮች ለደንበኞቻቸው በሚሰጡት የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ክፍያ ላይ የዋጋ ጭማሪ ሊያደርጉ ነው

በኢትዮጵያ የሚገኙ ባንኮች ለደንበኞቻቸው በሚሰጡት የዲጂታል እና ሌሎች አገልግሎታቸው ላይ የዋጋ ጭማሪ ሊያደርጉ እንደሆነ ኢትዮቲዩብ መረዳት ችሏል። ባንኮቹ በደንበኞቻቸው ላይ የዋጋ ጭማሪውን የሚያደርጉት መንግሥት ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች በራስ አቅም ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያችል ገቢ ለመሰብሰብ በማቀዱ ነው ተብሏል።

ከዚሁ ጉዳይ በተያያዘ ኢትዮቴሌኮም በአገልግሎቶቹ ላይ የዋጋ ጭማሪ ማድረጉን መዘገባችን ይታወሳል። ተቋሙ በዚህ ዓመት ብቻ ሁለት ጊዜ ባደረገው የዋጋ ማሻሺያ እስከ 700 ብር የሚደርስ ጭማሪ አድርጓል።

በተመሳሳይ መልኩ ባንኮችም ከኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በተፃፈላቸው ደብዳቤ፤ “በሀገሪቱ የሚከሰተውን ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች በራስ አቅም ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ሁሉም ባንኮች ከደንበኞች ላይ ክፍያዎችን በመሰብሰብ ለኢትዮጵያ አደጋ ስጋትና ምላሽ ፈንድ ፅ/ቤት ሂሳብ ገቢ እንዲያደርጉ” ታዝዘዋል።

ለአብነት አዋሽ ባንክ ለደንበኞቹ በላከው አጭር የጽሑፍ መልዕክት ከሚሰጠው ማንኛውም ዓይነት ብድር ላይ 1 በመቶ እና በዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ክፍያ ላይ ደግሞ 5 በመቶ ጨምሮ ክፍያውን እንደሚሰበሰብ አስታውቋል። ይህን አሠራር ከየካቲት ወር ጀምሮ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩንም ባንኩ ለደንበኞቹ ከላከው የጽሑፍ መልዕክት ላይ ተመልክተናል።

#Ethiopia #EthiopianBanks #EthiopianEconomy #AddisAbaba #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
1 3 2K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram