avatar
EthioTube
@ethiotube
21.02.2026 20:07
"የመከላከያ ሠራዊት ትግራይ ክልል በሚገኙ የቀድሞ ካምፑቹ ይገባል መባሉ ሐሰት ነው" የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር

የመከላከያ ሠራዊት "የሀገሪቱን ሉዓላዊ ግዛት ለማስከበር ወደ ትግራይ ክልል ይገባል ተብሎ" የተነገረው መረጃ ሐሰት ነው ሲል የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ሌቴናንት ጄነራል ታደሰ ወረደ የሚመሩት የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ይህን መግለጫ ያወጣው በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች የመከላከያ ሠራዊት "በኤርትራ የተያዙ የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛቶችን ለማስመለስ ወደትግራይ ክልል እንደሚገባ" እየተነገረ በመሆኑ ነው።

በዚህ መረጃ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ በፌደራል መንግስቱ መታዘዙ ተዘግቧል። ሆኖም አስተዳደሩ ዛሬ የካቲት 14/2018 ዓ.ም. በወጣው መግለጫ መረጃው ሐሰት መሆኑ ይታወቅልኝ ብሏል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ፤ ሐሰተኛ ያላቸው እና የተሰራጩት መረጃዎች የመከላከያ ሠራዊት "በቀድሞ የሰሜን ዕዝ ካምፖች እንዲሰፍር እንደተስማማ ተደርጎ በተለያዩ መንገዶች እየነገረ ነው” ብሏል።

እነዚህ የማኅበራዊ ሚዲያ መረጃዎች የተጣመሙ እና የተሳሳቱ መሆናቸዎን ገልጿል። እንዲህ ዓይነቱ መረጃ ወደ ኅብረተሰቡ የተሰራጨበት “ስትራቴጂ፣ ምንጩም ሆነ ሊያሳከው የተፈለገው ግብ ግልጽ ነው” ሲል በመግለጫው አመላክቷል።

#Ethiopia #Tigray #TPLF #TadesseWorede #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
1 2.1K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram