avatar
EthioTube
@ethiotube
17.02.2026 22:18
በጋሞ ዞን በተከሰተ ግጭት 15 ሰዎች ተገደሉ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ በተቀሰቀሰ ግጭት 15 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎችና አካባቢውን የወከሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ተናግረዋል። ግድያው የተፈጸመው ከትናንት በስቲያ እሑድ እና ትናንት ሰኞ በወረዳው ዛይሴ ወዘቃ እና ዛይሴ ደንብሌ በተባሉ ቀበሌያት በተቀሰቀሰ ግጭት ነው ፡፡

ለደኅንነታቸው ሲሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የዛይሴ ደንብሌ ቀበሌ ነዋሪ ግጭቱ ከትናንት በስቲያ አሑድ 10 ሰዓት ላይ ተከስቶ እስከ ትናንት ሰኞ ቀትር ድረስ መቀጠሉን ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡ በፖሊስ አጀብ ተሽከርካሪ ተጭነው በቀበሌው በማለፍ ላይ የነበሩ የጋሞ ዞን የፀጥታ አባላት “ድንጋይ ተወርውሮብናል” በሚል ምክንያት ግጭቱ መነሳቱን ነዋሪው ገልጸዋል።

“የጸጥታ አባላቱ ድንጋይ የወረወረውን ሰው ለመያዝ በሚል ወደ መንደሮች እና በየቤቱ በመግባት በከፈቱት ተኩስ ወላጅ አባታችንን ጨምሮ የአምስት ሰዎች ሕይወት አልፏል” በማለት እኒህ ነዋሪ መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል። የዛይሴ የምርጫ ክልልን በመወከል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ አብረሃም አሞሼ የፀጥታ አባላቱ በቀበሌያቱ ከፈቱት ባሉት ተኩስ በዛይሴ ወዘቃ ቀበሌ ሰባት እና በዛይሴ ደንብሌ ቀበሌ ደግሞ ስምንት ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል።

ከቀናት በፊት በተካሄደው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 5ተኛ ዓመት 6ተኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ የሥራ ሪፖርት ያቀረቡት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ፤ የክልሉን የፀጥታ ጉዳይ በሪፖርታቸው ጠቅሰዋል።

#Ethiopia #GamoZone #Gamo #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
2 2.3K

Обсуждение 2

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram