avatar
EthioTube
@ethiotube
17.02.2026 21:46
ከዚህ በፊት የመከላከያ ሠራዊት አባል የነበሩ ዜጎች ሰራዊቱን በድጋሚ እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀረበላቸው

ከዚህ ቀደም የመከላከያ ሠራዊት አባል የነበሩ እና ወደሠራዊቱ መመለስ ለሚፈልጉ ዜጎች ጥሪ ቀርቦላቸዋል። የመከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው ማስታወቂያ “ከአሁን በፊት የመከላከያ ሠራዊት አባል የነበሩ በተለያየ ምክንያት ከሠራዊቱ የወጡ” እና “ተመልሶ ሠራዊትን ለማገልገል ፍላጎት እና ቁጭት እያላቸው እስካሁን የመመለስ ዕድል ያላገኙ አባላትን” መመዝገብ እፈልጋለሁ ብሏል።

ሚኒስቴሩ ጥሪ ያደረገላቸው የቀድሞ የሠራዊቱ አባላት ከ 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ተቋሙ ሳያሰናብታቸው በራሳቸው ጊዜ የወጡ ዜጎችን ነው። በሀገር አቀፍ ደረጃ የተደረው ጥሪ “አሁን ካለው ወቅታዊ ሁኔታ በመነሳት የፅንፈኞቹ ፋኖና ሸኔ አባል አለመሆናቸው” አንዱ መስፈርት ነው። በተጨማሪ “በማንኛውም ፀረ-ሕዝብ ተግባር ያልተሳተፉ እና ከፖለቲካ ድርጅት ወገንተኝነት ነፃ የሆኑ” ዜጎች መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።

በአዲስ አበባ የሚገኙ የቀድሞ አባላት አምባሳደር አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ብሔራዊ ተጠባባቂ ኃይል ማደራጃ እና ማስተባበሪያ ቢሮ መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል። በክልል ለሚገኙት ደግሞ የዞን፣ የወረዳ አስተዳደር ጸጥታ ቢሮ አሊያም ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ምዝገባ ማድረግ ይችላሉ መባሉን ተመልክተናል።

የመከላከያ ሚኒስቴር ምዝገባውን ያፈጸሙ የምልስ ሠራዊት አባላት ወደ ማሰልጠኛ ማዕከላት የሚጓዙበት እና የሚገቡበት ቀን እገልጻለሁ ሲል ባሰራጨው የቅጥር ማስታወቂያ ላይ ገልጿል።

#Ethiopia #EthiopianArmy #ENDF #EthiopianNationalDefenseForce #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
1 1.7K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram