avatar
EthioTube
@ethiotube
15.02.2026 10:17
ከሁለት ወር በፊት በሚሰጣቸው አገልግሎቶች የዋጋ ጭማሪ አድርጎ የነበረው ኢትዮቴሌኮም በድጋሚ ዋጋ ጨመረ

የዋጋ ጭማሪ ያደረግሁት “ለብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ የሚውል መዋጮ መሰብሰብ ስለጀመርሁ ነው” ኢትዮ ቴሌኮም

ኢትዮቴሌኮም በሚሰጣቸው አገልግሎቶች በዚህ ዓመት ብቻ ሁለት ጊዜ የዋጋ ጭማሪ አደረገ። ባለፈው የታኀሳስ ወር ላይ በአንድ ጊዜ እስከ 500 ብር ጭማሪ ያደረው ተቋም በዚህ ወር በድጋሚ ጭማሪ ማድረጉ ታውቋል።

ሀገር በቀሉ የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት ታኀሳስ 20/2018 ዓ.ም. የዋጋ ጭማሪውን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፤ ተለያዩ ምክንያቶች እየጨምሩ ያሉ “የካፒታል እና የሥራ ማስኬጃ ወጪዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት” የዋጋ ጭማሪ አድርጊያለው ማለቱ አይዘነጋም።

በወቅቱ በተደረገው “የዋጋ ማስተካከያ” 1300 ብር ሲሸጥ የነበረው ወርሃዊ ያልተገደበ የኢንተርኔት ጥቅል 500 ብር ጨምሮ 1800 ብር ተደርጎ ነበር። ወርሃዊ ያልተገደበ የኢንተርኔት እና የድምፅ ጥቅል ወደ 2375 ብር ከፍ ተደርጓል። 65 ብር ሲሸጥ የነበረው ዕለታዊ ያልተገደበ የኢንተርኔት ጥቅል 20 ብር ጨምሮ 85 ሆኖ ነበር።

አሁን ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ በተደረገው የዋጋ ጭማሪ 1800 ብር የነበረው ወርሃዊ ያልተገደበ የኢንተርኔት ጥቅል 2000 ብር ገብቷል። በ 2375 ብር ይሸጥ የነበረው ወርሃዊ ያልተገደበ የኢንተርኔት እና የድምፅ ጥቅል 275 ብር ጨምሮ 2,650 ብር ሆኗል። ወደ 85 ከፍ የተደረው ዕለታዊ ያልተገደበ የኢንተርኔት አገልግሎትም ዋጋው ጨምሮ 95 ብር ገብቷል። በተመሳሳይ መልኩ ሳምንታዊ ጥቅል ላይም የዋጋ ጭማሪው ተደርጓል።

#Ethiopia #EthioTelecom #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
3 1 2.1K

Обсуждение 3

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram