avatar
EthioTube
@ethiotube
14.02.2026 23:52
የቅድመ ጋብቻ ስልጠናን ያልወሰደ ማንኛውም ሰው ወደ ጋብቻ መግባት አይችልም የተባለው ሐሰት ነው ሲል የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

ከትዳር በፊት የቅድመ ጋብቻ ስልጠናን ያልወሰደ ማንኛውም ሰው ወደ ጋብቻ መግባት አይችልም የተባለው ሐሰት ነው ሲል የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስተባበለ።

‎ሚኒስቴሩ በጉዳዩ ላይ ባወጣው መግለጫ "ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የፍቺ ቁጥር ለመቀነስ፣ የቅድመ ጋብቻ ስልጠና ሰርተፊኬት ሳይዝ ማንም ሰው ወደ ጋብቻ እንዳይገባ የሚያደርግ አሰራር ሊጀምር ነው" በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ ያለው ዘገባ የተሳሳተ ነው ብሏል።

በሸገር ራዲዮ የተሰራጨው ዘገባ፤ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የአረጋውያንና ቤተሰብ ጉዳዮች ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ሮበሌን ዋቢ በማድረግ አሠራሩ በሚቀጥለው ዓመት ተግባራዊ እንደሚደረግ ገልፆ ነበር።

‎ የቅድመ ጋብቻ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት አስፈላጊ ነው ያለው ሚኒስቴሩ ሆኖም፤ "ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ አስገዳጅ ለማድረግ ያለመ የአሰራር ማዕቀፍ እያዘጋጀ ነው" የሚለው ፍፁም የተሳሳተ መረጃ በመሆኑ ሊታረም ይገባል ሲል አስታውቋል።

#Ethiopia #AddisAbaba #MarriageLaw #FamilyValues #EthiopianNews #EthioTube #Africa
1 7 2.1K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram