avatar
EthioTube
@ethiotube
13.02.2026 22:25
የሰውነቷን መወፈር በተመለከተ  ቲክቶክ ላይ በሚደርሳት የቀልድ እና ፌዝ አስተያየት ምክንያት ራሷን ያጠፋችው የ 13 ዓመት ታዳጊ

"አባቴ ሁሉን ነገር ሰጥተህ አሳድገኸኛል። ደስተኛ ነበረኩ በዚህ ምድር ላይ ያላየሁት ነገር የለም፤ሁሉን ዐይቻለሁ። ምንም አዲስ ነገር የለም ራስ ወዳድ በመሆኔ ይቅርታ አድርግልኝ ጥሩ ቦታ ስለምሔድ ለእኔ ደስተኛ ሁን" ታዳጊዋ ራሷን ከማጥፋቷ በፊት ለአባቷ የፃፈችው ደብዳቤ

ፊዮሬላ ነብዩ የተባለች  የ13 ዓመት ታዳጊ በሰውነት ቅርጿ ላይ በሚሰነዘርባት ትችት፣ፌዝ እና ቀልድ ምክንያት ራሷን ልታጠፋ እንደቻለች ተገልጿል።ከመሞቷ በፊት ባሉት ወራት ፊዮሬላ ክብደቷ ጨመሮ ነበር። ይህ ውፍረቷ በእኩዮቿ ዘንድ የፌዝ ምንጭ ሆነ።በትምህርት ቤትም ሆነ በበይነ መረብ የሚሳለቁባት፣ የሚያፌዙባት ሰዎች ነበሩ።

ይህ ጉዳይ እየዋለ ሲያድር በራስ መተማመንዋን እንደሸረሸረው ቢቢሲ በዘገባው አስነብቧል።
ፊዮሬላ ሰውነቷን አስመልክቶ የምትሰማው አስተያየት ምቾት እንዳልሰጣት ለእህቶቿ እና ለጓደኞቿ ነግራቸዋለች።

"ክብደት እየጨመርኩ ነው"፤ "ራሴን አልወድም" ብላቸዋለች።ወዲያው ደሞ እየቀለድኩ ነው" ስትል ጉዳዩን ለማለዘብ ትሞክራለች።

በመጨረሻዎቹ ቀናት የፊዮሬላ ባህሪ ቀስ በቀስ መለወጥ ጀመረ። አንድ ቀን ፊዮሬላ  እንደተለመደው በማለዳ አልነቃችም። በዚህ ሰዓት ወደመኝቷ ቤቷ ያመራው አባቷ የ13 ዓመት ዕድሜ ያላት ልጁ ተሰቅላ እንዳገኛት ተዘግቧል።

ፊዮሬላ ከመሞቷ በፊት አሥር ደብዳቤዎችን ጽፋ ነበር። ደብዳቤዎቹ ለወላጆቿ፣ ለእህት እና ለወንድሟ እንዲሁም ለጓደኞቿ የተጻፉ ናቸው።
ታዳጊዋ ልደቷ ሊከበር ሰባት ሳምንታት ሲቀሩት ነበር ራሷን አጠፋች።

#Ethiopia #TikTok #EthiopianKids #EthiopianChildren #SocialMedia #EthioTube #Africa
1 3 2.1K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram