avatar
EthioTube
@ethiotube
13.02.2026 19:58
እየጨመረ የመጣውን የፍቺ ቁጥር ለመቀነስ የቅድመ ጋብቻ ስልጠና ሰርተፊኬት ያልያዘ ሰው ወደ ጋብቻ እንዳይገባ የሚያደርግ አሰራር ሊጀምር ነው

በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የፍቺ ቁጥር ለመቀነስ የቅድመ ጋብቻ ስልጠና ሰርተፊኬት ያልያዘ ማንኛውም ሰው ሰው ወደ ጋብቻ እንዳይገባ የሚያደርግ አሰራር ሊጀመር መሆኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል።ይህ አዲስ አሰራር ከሃይማኖት ተቋማትና ከሃገር ሽማግሌዎች ጋር በመመካከር ሥራ ላይ የሚውል ነው ሲል ሸገር ራዲዮ ዘግቧል።

ይህን አሠራር በሚቀጥለው ዓመት ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅት መደረጉን በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የአረጋውያንና ቤተሰብ ጉዳዮች ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ሮበሌ ተናግረዋል። ለብዙ ትዳሮች መፍረስ ዋነኛው ምክንያት ስለ ትዳር ያለው የግንዛቤ ዕጥረት ነው ያሉን አቶ ተስፋዬ፤ ይህንንም ችግር ለመፍታት የሥልጠና ማኗሎችን መዘጋጀታቸውን አስረድተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጄንሲ በቅርቡ ባወጣው መረጃ መሰረት የትዳር ፍቺ ከአለፉት ዓመታት አንፃር 54 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። ለተጋቢዎች የቅድመ ጋብቻ ሥልጠና ከመስጠት በተጨማሪ በቤተሰብ ጉዳይ ላይ የሚሰሩ ተቋማት ሥራቸውን ውጤታማ ለማድረግ የጋራ ፎረም እንደተመሠረተ ሥራ አስፈፃሚው አሳውቀዋል።

ፎረሙ በቤተሰብ አስተዳደር በኩል ያሉ የአሠራር ክፍተቶችን ለመሙላት እና በመንግስት በኩልም መሰራት ላለባቸው ነገሮች ምክረ ሃሳብና ጥቆማ ለመስጠት የሚያስችል ነው ተብሏል።

#Ethiopia #AddisAbaba #MarriageLaw #FamilyValues #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
6 1.7K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram