avatar
EthioTube
@ethiotube
13.02.2026 19:26
የሱዳን አማፂያን የሚሰለጥኑበት ምስጢራዊ ካምፕ በኢትዮጵያ መገንባቱን በምረመራ ዘገባ የገለጠው ሮይተርስ የዘገባ ፈቃዱ ተነጠቀ

ኢትዮጵያ ከተባበሩት ዐረብ ኢመሬትስ ጋር በመሆን የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል የተሰኘው ታጣቂ ቡድን የሚሰለጥንበት ካምፕ በቤኒሻንጉልጉሙዝ ክልል መገንባቱን የሚገልጽ የምርመራ ዘገባ ሮይተርስ የተሰኘው የዜና ምንጭ ካሰራጨ በኋላ የኢትዮጵያ መንግሥት የዘገባ ፈቃዱን እንደነጠቀው ተሰምቷል።

ሮይተርስ በምርመራ ዘገባው የደህነነት፣የዲፖሎማቲክ አባላትን፣ባለሥልጣናትን እና የሳተላይት ምስል በመጠቀም ተገንብቷል ስላለው ምስጢራዊ ካምፕ ሰፊ መረጃን አጋርቷል። ከአሶሳ ኤርፖርት 53 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተገባው ካምፕ በርካታ ኢትዮያውያን ምልምሎችን ጭምር የሚያሰለጥኑበት ቢሆንም ከጥር ወር አንስቶ 4,300 የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኅይል አባላት ስልጠና ወስደዋል ሲል ዘገባው አመላክቷል። በተጨማሪ የወታደራዊ ስልጠና የበጀት ሆነ የሎጀስቲክስ ምንጭ ደግሞ የተባበሩት ዐረብ ኤሜሬትስ እንደሆነችም ያትታል። ምንም እንኳን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ እጃችን የለበትም በማለት ስለጉዳዩ አናውቅም በማለት ቢያስተባብልም።

የኢትዮጵያ መንግሥት ግን እስካሁን በጉዳዩ ላይ ይፋዊ ምላሽ ባይሰጥም፤ ይህ በዓለም አቀፍ ማኀበረሰቡ ዘንድ መነጋገሪያ የሆነው ዘገባ ከተሰራጨ በኋላ የሮይተርን የዘገባ ፈቃድ እንደወሰደ ተሰምቷል። በዚህ ሳምንት የሚካሔደውን የአፍሪካ ኀብረት ስብሰባ ለመታደም የዘገባ ባጅ የወሰዱ የሚዲያው ጋዜጠኞችም የተሰጣቸውን ባጅ እንዲመልሱ ተደርገዋል ተብሏል።

#Ethiopia #Press #Sudan #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa #Reuters
1.9K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram