avatar
EthioTube
@ethiotube
10.02.2026 19:40
በኢትዮጵያ የሱዳን አማፂ ኃይሎች የሚሰለጥኑበት “ሚስጥራዊ ካምፕ” መገንባቱ ተሰማ

ከሱዳን መንግሥት ጋር እየተፋለመ ያለው የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል የተሰኘ ታጣቂ ቡድን የሚሰለጥንበት “ሚስጥራዊ ካምፕ” በኢትዮጵያ ተገንብቷል ሲል ሮይተርስ በሰራው የምርመራ ዘገባ ገልጿል።

በጄነራል መሐመድ ሐምዳን ደጋሎ ወይም ሄሜቲ የሚመራው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል አባላት የሚሰለጥኑበት ነው የተባለው ወታደራዊ ካምፕ የገነባችው የተባበሩት ዐረብ ኤምሬትስ መሆኑን ስማቸው ያልተገለጸ አንድ የኢትዮጵያ ባለሥልጣን ጭምሮ ከስምንት የመረጃ ምንጮች ሰምቻለሁ ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።

ከኢትዮጵያ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት እንዳላት የሚነገረው ኤሜሬትስ የሎጀስቲክስ እና የወታደራዊ ሥልጠና ወጪዎችንም እንደምትሸፍን በዘገባው ተመላክቷል። ሮይተርስ ሳተላይት በመጠቀም በቤኒሻንጉልጉሙዝ ክልል መንጌ በተሰኘ አካባቢ የተገነባውን ወታደራዊ ካምፕ የሚያሳዩ ምስሎችን ይፋ አድርጓል።

ከዋና ከተማዋ አሶሳ ኤርፖርት 53 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተገባው ካምፕ በርካታ ኢትዮያውያን ምልምሎችን ጭምር የሚያሰለጥኑበት ቢሆንም ከጥር ወር አንስቶ 4,300 የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኅይል አባላት ስልጠና ወስደዋል ተብሏል።

በተጨማሪ ከደቡብ ሱዳን የመጡ ዜጎችም በካምፑ ስልጠና እንደሚወስዱ ተገልጿል። ይህ የሰራዊት ማሰልጠኛ ካምፕ 10,000 ሰዎችን የመያዝ አቅም ያለው መሆኑ ተገልጿል።

ይህን ካምፕ በማስገንባቱ እና በመቆጣጠር ረገድ ኃላፊነቱን የተረከቡት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የመረጃ ዋና መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ጄኔራል ጌታቸው ጉዲና መሆናቸው በዘገባው ላይ ተመላክቷል።

#Ethiopia #Sudan
1 3 2.3K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram