avatar
EthioTube
@ethiotube
08.02.2026 00:43
“ከመንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት በመፈፀሜ ወንድሜን ገደሉት” ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ

በቅርቡ ከመንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት የፈጸሙት ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ በበቀል ሳቢያ ወንድማቸው መገደሉን ተናገሩ።ወንድሜ ቢገደልም “እኔ ግን ሀገር አድኛለሁ ደስታ ይሰማኛል” ብለዋል። በአማራ ክልል በትጥቅ ትግል ሲንቀሳቀስ የነበረው የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋህድ) አመራር የነበሩት ማስረሻ፤ ይህን የተናገሩት ከሀገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቭዥን ጋር በነበራቸው ቆይታ ነው።

“የአማራ ህዝብ እየደረሰበት ያለውን በደል” በመቃወም ከሶስት ዓመት በፊት ወደ ትጥቅ ትግል እንደገቡ የሚናገሩት ካፒቴን ማስረሻ የትጥቅ ትግሉ በሌሎች የውጭ ኃይሎች መጠለፉን በነበራቸው ቆይታ አብራርተዋል። ማስረሻ የውጭ ኃይሎች ሲሉ የጠሯቸው ግብጽን እና የሻዕቢያን መንግሥት ነው። ጽምዶ በሚል ስያሜ “በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ኃይል እና ኦነግ ሸኔ ጥምረት መፍጠራቸውንም በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።

“ግብጽ በዋናነት ፋይናንስ መድባ እየሰራች ነው። ህወሓት፣ ሻዕቢያ፣ ኦነግ ሸኔ እና አማራ አካባቢ ያለው አፋብን [ብሎ] ራሱን ሰይሞ እየተንቀሳቀሰ ያለ ቡድን የራሳቸውን ጥምረት ፈጥረዋል። ጽምዶ በሚል። የመጨረሻ ግቡ የዚህ ጥምረት ምንድነው ካልህ ሀገር ማፍረስ ነው” በማለት ስለ ጥምረቱ ዓላማ አስረድተዋል። ካፒቴን ማስረሻ አክለውም “ተራ ዝምብሎ የመበጥበጥ እና የአሸባሪነት ተግባር ነገር እንጂ ሕዝብ ይዞ፣ የሕዝብን ጥያቄ ይዞ የመሔድ ነገሮች አይታይም” በማለት ጽምዶ ስላሉት ግንኙነት ተናግረዋል።

ይህን የትግል አካሔድን በመቃወም፤ የአማራ ሕዝብ ጥያቄን በድርድር ለማስመለስ እና ሰላማዊ አማራጮችን ለመከተል መወሰናቸውን የሚናገሩት ማስረሻ፤ በዚህ እርምጃቸው የተቃወሙ አካላት በቤተሰባቸው ላይ የበቀል እርምጃ መወሰዳቸውን ተናግረዋል።
1 3 2.5K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram