avatar
EthioTube
@ethiotube
06.02.2026 20:49
በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ብቻ እስከ 1,000 ብር የጨመረው ፈሳሽ የምግብ ዘይት

ፈሳሽ የምግብ ዘይት ከጊዜ ወደ ጊዜ ዋጋው እየጨመረ ነው። ባለፉት ሁለት ሳምንታት እስከ 1400 ብር ይሸጥ የነብረው 5 ሊትር ዘይት አሁን ላይ 1,000 ብር ጨምሮ 2400 እየተሸጠ ይገኛል። ይህ ከፍተኛ የጋዋ ጭማሪ ከጅምላ አከፋፋዮች አንስቶ እስከ ቸርቻሪዎች ድረስ የተያያዘ መሆኑ ተመልክቷል።

ፎርቹን ጋዜጣ በጉዳዩ ላይ በሠራው ተመሳስይ ዘገባ የዘይት ዋጋ የመናሩ ምክንያት ምርቱን ከውጭ የሚያስገቡ ነጋዴዎች ዋጋ በመጨመራቸው ነው ሲሉ በመርካቶ አካባቢ የሚገኙ የጅምላ አከፋፋዮች ነግረውኛል ብሏል። ከ ሁለት ሳምንት በፊት በአዲስ በፊት በ 1700 እና 1800 ብር ሲሸጥ የነበረው አምስት ሊትር ዘይት እንደ ምርቱ ዓይነት እስከ 1,000 ብር ጨምሯል።

ኦርኪድ የተሰኘው 5 ሊትር ዘይት 2,200 ብር እየተሸጠ ይገኛል። 1,750 ብር ይሸጥ የነበረው ባድሪያ የተሰኘው ዘይት ደግሞ 400 መቶ ብር ጨምሮ 2,150 ብር ገብቷል። 1,700 ብር የነበረው ሰንፍላዎር ፈሳሽ የምግብ ዘይት በሳምንታት ውስጥ 2,100 ብር ገብቷል። ከዚህ በተጨማሪ ኦማር የተባለው ዘይት በ2,400 ብር ለገበያ ቀርቧል።

በዘይት ላይ የታየው ከፍተኛ ጭማሪ የነዋሪውን ሕይወት በእጅጉ እንደፈተነው ዘገባው አመላክቷል። በጉዳዩ ላይ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ካለዘይት የተሰራ ምግብ መመገብ የግድ እንደሆነባቸው ተናግረዋል። የዋጋ ጭማሪው በተመሳሳይ መልኩ ባለ 3 ሊትር ፈሳሽ ዘይት ላይም በመሆኑ አቅም ያላቸው ባለ 1 ሊትሩን ዘይት በ 450 ብር ገዝተው እየተጠቀሙ መሆናቸውን ተናግረዋል።

አስመጪዎች እንደገለጹት ከሆነ ለምርቱ መወደድ ዋና መንስዔ “የውጭ ምንዛሬ እጥረት እና ለተለዩ የሥራ እንቅስቃሴዎች የሚያወጡት ዋጋ መጨመሩ ነው ብለዋል።

#Ethiopia
1 3 2.1K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram