avatar
EthioTube
@ethiotube
03.02.2026 20:53
“በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ፀብ የተጀመረው በትግራይ ጦርነት ወቅት የኤርትራ ሠራዊት ንጹኃን በጅምላ ሲረሽን እና ንብረት ሲዘርፍ ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

በወቅቱ ለኤርትራ መንግሥት “የትግራይ ሕዝቤን አታጎሳቅሉ፣ ሀብቱን አትዝረፉ” ብዬ መልዕክት ልኬያለሁ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ፀብ የጀመረው በትግራይ ጦርነት ወቅት የኤርትራ ሰራዊት “ወጣቶችን በጅምላ ሲረሽን”፣ “የግለሰቦችን ቤት ማፍረስ ሲጀምር” እና “ፋብሪካዎችን ሲነቅል እና ሲያፈራርስ” መሆኑን ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት ዛሬ ማክሰኞ ጥር 26/2018 ዓ.ም. በፓርላማ ተገኝተው ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ እና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው። ዐቢይ ማብራሪያ ከሰጡባቸው በርከት ያሉ ጉዳዮች ውስጥ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ስለተፈጠረው አለመግባባት አንዱ ነው። በሁለቱ ሀገራት መካከል ቅራኔ የተፈጠረው በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ምክንያት እንደሆነ ተደጋግሞ ይነገራል። ይሁን እንጂ ዐቢይ በዛሬ ማብራሪያቸው የፀቡ መነሻ የኤርትራ ሰራዊት ወደ ትግራይ ክልል ገብቶ በፈጸማቸው ወንጀሎች ነው ሲሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኤርትራ ሰራዊት ተፈጽሟል ብለው ከዘረዘሯቸው ወንጀሎች መካከል ንጹኃን መረሸን፣ የግለሰብ መኖሪያ ቤቶችን ማፍረስ ፋብሪካዎችን ማውደም እና መስረቅ የሚሉት ይገኙበታል።

“አንዳንድ ሰዎች በኢትዮጵያ እና ከኤርትራ መካከል ችግር የተፈጠረው የኢትዮጵያ መንግሥት የቀይ ባሕር ጥያቄ ስላነሳ ነው ይላሉ፣ ያስባሉ፣ ይተነትናሉ ግን አይደለም። ፀቡ የተጀመረው ብዙዎች እንደሚያስቡት የቀይ ባሕር ጉዳይ ሲመጣ አይደለም።


#Ethiopia #Eritrea #Tigray
3 2.7K

Обсуждение 3

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram