avatar
EthioTube
@ethiotube
02.02.2026 20:00
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጀነራል ታደሰ ወረደ፤ በክልሉ ግጭት የተቀሰቀሰበት ምክንያት የትግራይ ኃይሎች ወደ ጸለምት አካባቢ ለመግባት በሚንቀሳቀሱበት ወቅት የተፈጠረ መሆኑን ተናገሩ

ከሰሞኑ በትግራይ ኃይሎች እና በፌደራል መንግሥት መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት፤ የትግራይ ኃይሎች ወደ ጸለምት አካባቢ ለመግባት በሚንቀሳቀሱበት ወቅት የተፈጠረ መሆኑን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ጀነራል ታደረ ወረደ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ ይህን የተናገሩት ጉዳዩን አስመልክቶ በትግራይ ቴሌቭዥን በሰጡት ማብራሪያ ላይ ነው።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባለፈው አርብ ጥር 22/2018 ዓ.ም. ባወጥው መግለጫ፤ በትግራይ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች መካከል በሚገኙ "አንዳንድ አዋሳኝ አካባቢዎች" ግጭቶች መቀስቀሳቸውን አረጋግጧል። ኮሚሽኑ በመግለጫው ከአንድ ሳምት በፊት ጥር 17/2018 ዓ.ም. ጀምሮ ግጭት ከተካሄደባቸው ቦታዎች አንዱ የትግራይ እና አማራ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ ከሚያነሱበት አካባቢዎች አንዱ በሆነው “ጸለምት/ጠለምት” መሆኑን አመላክቷል። በዚህ አካባቢ የጀመረው ግጭት ምክንያት ከተፈናቃዮች አለመመለስ ጋር የሚገናኝ እንደሆነ ጀነራል ታደሰ ተናግረዋል።

“ወደ ላይኛው ጸለምቲ እና በትንሹም ወደ ታችኛው ፀለምቲ የተወሰነ ኃይል እንዲሻገር ተወስኗል” ሲሉ የታጣቂዎቹ እንቅስቃሴ በጊዜያዊ አስተዳደሩ ውሳኔ የተከናወነ እንደሆነ ጠቁመዋል። ይህ ውሳኔ የተወሰነው ከተፈናቃዮች አለመመለስ ጋር በተገናኘ እንደሆነም ገልጸዋል ሲል ቢቢሲ በዛሬ ዘገባ አመላክቷል።

ጀነራል ታደሰ ጸለምት አካባቢ "ሊፈርስ የሚገባው ሕገ-ወጥ አስተዳደር እየተጠናከረ" በመሄዱ ምክንያት ተደናቅፏል ያሉትን "የማንነት አደጋም" በምክንያትነት ጠቅሰዋል።

#Ethiopia #Tigray
2 2.4K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram