avatar
EthioTube
@ethiotube
31.01.2026 21:29
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚቀጥለው ማክሰኞ ፓርላማ ሊቀርቡ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ማክሰኞ ጥር 26/2018 ዓ.ም. በፓርላማ ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ እንደሚሰጡ ተሰምቷል።

በሕገ መንግሥቱ እና በምክር ቤቱ የአሠራርና የአባላት የሥነ- ምግባር ደንብ መሠረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትሩን እና ሌሎች የፌዴራሉ መንግሥት ባለሥልጣናትን ለጥያቄ የመጥራት፣ የሕግ አስፈፃሚውን አካል አሠራር የመመርመር፣ የመከታተልና የመቆጣጠር ሥልጣን አለው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ በፓርላማ በሚኖራቸው ቆይታ የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በቀጥታ ሥርጭት በሚተላለፈው ውይይት፤ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች ይገኛሉ ተብሏል።

#Ethiopia #EthiopianParliament #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa #AbiyAhmed #PMAbiy
1 2.2K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram