avatar
EthioTube
@ethiotube
31.01.2026 21:11
በትግራይ ክልል ተፈጽሟል በተባለ የድሮን ጥቃት የሰው ሕይወት አለፈ

በፌደራል መንግሥት እና በትግራይ ኃይሎች መሀል በድጋሚ ግጭት ተቀስቅሷል መባሉ ከተሰማ በኋላ በድሮን ጥቃት የሰው ሕይወት ማለፉ ተነግሯል። በክልሉ እንትጮ እና ገንዳበታ በተባሉ አካባቢዎች የጭነት መኪና ላይ በተፈጸመው የድሮን ጥቃት የአንድ ሰው ሕይወት ሲያልፍ አንድ ሰው ደግሞ መቁሰሉ ተሰምቷል።

ይህን ጥቃት አስመልክቶ የተለያዩ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ሽፋን ሰጥተውታል። ምንም እንኳን ከፌደራል መንግሥት ሆነ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጦርነት ስለመጀመሩ በይፋ አላሳወቁም። ሆኖም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ካለፈው ሳምንት እሁድ ጥር 17/2018 ዓ.ም. ጀምሮ በትግራይ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች መካከል በሚገኙ አንዳንድ አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭቶች መቀስቀሳቸውን አስታውቋል።

የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ በመግለጫው ግጭት ተካሔዶበታል ሲል ከጠቀሳቸው አካባቢዎች አንዱ የትግራይ እና አማራ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ የሚያነሱበት “ጸለምት/ጠለምት” የተሰኘው ሥፍራ ነው። በተጨማሪ በመጋሌ እና አብአላ አካባቢዎች የተከሰቱ ግጭቶችን ተከትሎ የሰዎችን የሕይወት፣ የአካል ደኅንነት፣ ነጻነት እና ንብረት መብቶች ሥጋት ላይ የሚጥሉ ሁኔታዎች መፈጠራቸውን ኢሰመኮ አስታውቋል።

በዚህ ሁኔታ በቀጠለው ግጭት “የፌደራል መንግሥት” የድሮን ጥቃት በማድረስ ሁለት የጭነት አይሱዙ መኪናዎችን እንዳወደመ አልጀዚራ ዘግቧል። የድሮን ቦምቡ ያረፈው "በመኪናዎቹ ጋቢና" ላይ መሆኑን የእንትጮ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ተስፋይ አማረ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዚህ ጥቃት አንድ አሽከርካሪ ሕይወቱ እንዳለፈ እና የተሽከርካሪው ረዳት ደግሞ ጉዳት ደርሶበት ወደ ሆስፒታል መወሰዱን አስረድተዋል።

#Ethiopia #Tigray
2 1.9K

Обсуждение 2

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram