avatar
EthioTube
@ethiotube
31.01.2026 19:47
የመከላከያ ሠራዊት ዩኒፎርም በመልበስ እና ሀሰተኛ መታወቂያ በመያዝ ሰዎችን አግተው ዘረፋ ሲፈጽሙ የነበሩ ተጠርጣሪዎች ተያዙ

“ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ለማምለጥ ሲሞክሩ ገደል ውስጥ ገብተው የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል”

መከላከያ ሠራዊት ዩኒፎርም በመልበስ እንዲሁም ሀሰተኛ መታወቂያ በመያዝ ሁለት የሆላንድ ዜጎችን እና ሁለት ኢትዮጵያንን አግተው ሲዘርፉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ። ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ወንጀሉን ሲፈጽሙ እጅ ከፍንጅ ተይዘው ነው ተብሏል።

ተጠርጣሪዎቹ ያገቷቸው የውጭ የውጭ ዜጎች እና ኢትዮጵያውያን ላይ የዝርፊያ ወንጀል በመፈጸም ላይ እንዳሉ፤ እንጦጦ ፓርክ አካባቢ በስራ ስምሪት ላይ የነበሩት ምክትል ኢንስፔክተር በሪሁን ፈንቴ እጅ ከፍንጅ ይዘው ለጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ማስረከባቸው ፖሊስ ገልጿል።

ምክትል ኢንስፔክተር በሪሁን የፌደራል ፖሊስ የትራፊክ ቁጥጥርና የአደጋ ምርመራ መምሪያ ባልደረባ መሆናቸው ተመላክቷል። ወንጀሉን ሲፈጽሙ ከነበሩ ሰዎች ውስጥ ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ለማምለጥ ሲሞክሩ ገደል ውስጥ ገብተው የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲል የፌደራል ፖሊስ ባሰራጨው መረጃ ላይ አሳውቋል።

#Ethiopia #EthiopianFederalPolice #AddisAbaba #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
1 1.2K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram