avatar
EthioTube
@ethiotube
29.01.2026 18:41
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ትግራይ ክልል የሚያደርገውን በረራ ማቋረጡ ተሰምቷል

የበረራ መቋረጡ “በክልሉ በሚገኙ ባንኮች እና የንግድ ተቋማት ላይ ውጥረት አስከትሏል”

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ትግራይ ክልል የሚያደርገውን በረራ ማቋረጡ ተሰምቷል። የአየር መንገዱ በረራውን ማቋረጡ የተሰማው የትግራይ ኃይል እና የፌደራል መንግሥት በድጋሚ ግጭት ውስጥ ገብተዋል መባላቸው ከተዘገበ በኋላ ነው። በሁለቱ ኃይሎች እንደ አዲስ የተከሰተው ግጭት በአማራ እና ትግራይ ክልል አጎራባች አካባቢዎች ነው።

ዓለም አቀፉ የዜና ምንጭ አልጀዚራ በጉዳዩ ላይ በሠራው ዘገባ “በምዕራብ ትግራይ ፀለምት በተሰኘው አካባቢ ግጭት መቀስቀሱን” አመላክቷል። የኤ አፌፍ ፒሲን ዘገባ ዋቢ ያደረገው መረጃ በግጭቱ ሳቢያ በክልሉ የተለያዩ ከተማዎች የሚደረገው በረራ መቋረጡን የደህንነት እና የዲፕሎማቲክ ምንጮች መናገራቸውን ያትታል።

የጀርመን ድምፅ በዚሁ ጉዳዩ ላይ በሰራው ዘገባ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደትግራይ ክልል በረራ ማቋረጡን አረጋግጧል። ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ በረራ መቋረጡን ከሰሙ በኋላ ነገሮች በፍጥነት እየተለዋወጡ መሆኑን ከክልሉ ከነዋሪዎች ተሰምቷል “በተለይ የምግብ እና ምግብ ነክ ቁሳቁሶች መሸጫ የገበያ አካባቢዎች እንቅስቃሴ ጎልቶ እንደሚታይ” የመቐለ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ በመቐለ ከተማ የሚኖሩ የመንግስት ሠራተኛ “የአውሮፕላን በረራ መቋረጡን ተከትሎ አዲስ አበባ የሚገኙ ዘመዶቻቸው ወደ መቀሌ ለመመለስ መቸገራቸውን ተናግረዋል” ሲል ዘገባው ገልጿል። ነዋሪዋ አክለውም “የበረራው መቋረጥ በባንኮች እና የንግድ ተቋማት አካባቢ ውጥረት ማስከተሉንም” አመላክተዋል።


#Ethiopia #Tigray #EthiopianAirlines
2 2 2.3K

Обсуждение 2

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram