avatar
EthioTube
@ethiotube
27.01.2026 19:56
1,800 ሰዎችን በሕገ-ወጥ መንገድ በማዘዋወር ከ 2.1 ቢሊዮን ብር በላይ የሰበሰቡ 22 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ተመሠረተ

ተከሳሾቹ “ የ 2 ሰዎች ሕይወት እንዲያልፍ እና 15 ሰዎች የደረሱበት እንዳይታወቅ ያደረጉ ናቸው”

የፌደራል ፖሊስ 1800 ሰዎችን በሕገ-ወጥ መንገድ በማዘዋወር፤ የሁለት ሰዎች ሕይወት እንዲያልፍ እና 15 ሰዎች የደረሱበት እንዳይታወቅ ያደረጉ 22 ተጠርጣሪዎችን ምርመራ አጣርቶ ለፌደራል ዐቃቤ ሕግ መላኩን አስታውቋል። ከነዚህ ተጠርጣሪዎች ውስጥ በ ስድስቱ ላይ ክሱ የተመሰረተው በሌሉበት መሆኑ ተመላክቷል።

የፖሊስ የምርመራ መዝገብ እንደሚያስረዳዉ፤ ተጠርጣሪዎቹ “በሰዉ ልጅ ለመነገድ በማሰብ የወንጀል ቡድን በማደራጀት እና የቡድኑ አመራርና አባላት በመሆን የተሳተፉ ናቸው። በተጨማሪ ወንጀሉን ለመፈፀም ደላሎችን በመመልመል፤ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በማሰማራትና የሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር የወንጀል መረብ ዘርገተው ነበር ተብሏል።

በዚህ ተግባራቸው ሰዎች በሊቢያ በኩል ወደ አዉሮፓ ገብተዉ የተሻለ ኑሮ እንደሚኖሩ በሐሰተኛ ተስፋ በማሳመን ሲልኩ መቆየታቸውን የፖሊስ ምርመራ መዝገብ ያስረዳል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ወደ ሱዳን ድንበር የሚያጓጉዙ ተቀጣሪዎችን በማዘጋጀት በሕገ-ወጥ መንገድ ተጎጂዎችን ከሀገር ሲያስወጡ መቆየታቸውን የገለፀው ፖሊስ ሰዎች ከኢትዮዽያ ድንበር ከወጡ በኋላ በዘረጉት የወንጀል መረብ አማካኝነት ወደ ሊቢያ ወስደዉ በመጋዘኖች ሲያጉሩ ቆይተዋል ብሏል፡፡

#Ethiopia #HumanTrafficking #HumanTraffickers #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
1 2K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram