avatar
EthioTube
@ethiotube
24.01.2026 22:30
የኢትዮጵያ መንግሥት ዋዜማ ሬድዮ የተሰኘውን የበይነመረብ ሚዲያ አገደ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን ዋዜማ ራዲዮ የተሰኘውን የበይነ መረብ ሚዲያ "የሥራ ፍቃዱን" እና "ዕውቅናውን" እንደወሰደ ገልጿል።

ሚዲያው የሀገሪቱን "ሕገ-መንግሥት" እና "የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ" እንዲሁም "መመሪያዎች" እና "የሙያ ስነምግባር" አክብሮ ለመሥራት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ይህ እርምጃ እንደተወሰደበት ታውቋል።

ባለሥልጣኑ የሚዲያው ዘገባዎች የአገሪቱን "ብሔራዊ ጥቅም የሚጻረሩ"፣ "ሚዛናዊነት የሚጎድላቸው"፣ "የፌዴራልና የክልል መንግሥታት አስተያየትና ምላሽ" ያልተካተተባቸው ናቸው ሲል ወንጅሏል።

አክሎም፤ ሚዲያው ላይ በተደረገ ክትትል፣ ከዜጎች በተሰጡ አስተያየቶች እና ጥቆማዎች

"ሁከት ቀስቃሽ" እና "የአንድ ወገን" ዘገባዎችን ሲያሰራጭ እንደነበር አረጋግጫለሁ ብሏል። ለሚዲያው "ተደጋጋሚ የእርምት ግብረ መልስ" ስሠጥ ቆይቻለሁ ያለው ባለሥልጣኑ፣ ሆኖም መገናኛ ብዙኃኑ የተሠጠውን "አስተያያት" እና "የማስተከከያ እርምጃ" ባለመቀበሉ ፍቃዱን እንደወሰደ አመላክቷል።

ባለሥልጣኑ፣ ለዋዜማ ሬዲዮ ከሁለት ወር በፊት "የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ" ሠጥቶ እንደነበርም ጠቅሷል።

#Ethiopia #EthiopianMedia #EthiopianPress #WazemaRadio #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
1 2 1.7K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram