avatar
EthioTube
@ethiotube
24.01.2026 19:41
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ “አሁንም ሚግ 21 [የጦር ጀት] ላይ ያላችሁ” ሲሉ የጠሯቸውን ሀገራት አስጠነቀቁ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ “ቆማችሁ የቀራችሁ”፣ “ወደፊት መራመድ የምትቸገሩ” በማለት የጠሯቸውን ሀገራት አስጠነቀቁ። ዐቢይ ኢትዮጵያ ዘመናዊ የጦር ጀቶችን መታጠቋን ጠቁመው፤ “አሁንም ሚግ 21 [የጦር ጀት] ላይ ያላችሁ ሀገራት” ከኢትዮጵያ ጋር ተስማምቶ አብሮ ማደግ ብቻ ነው የሚያዋጣው በማለት ጠንካራ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ዛሬ ቅዳሜ ጥር 16/2018 ዓ.ም. የአየር ኃይልን 90ኛ ዓመት በማስመልከት በቢሾፍቱ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ነው። ዐቢይ በንግግራቸው አየር ኃይሉን ለማጠናከር ባለፉት ዓመታት ስለተከናወኑ ሥራዎች አብራርተዋል።

ምንም እንኳን አየር ኃይል 90 ዓመታት ቢሞላውም “በዕድሜው ልክ በቂ ተከታታይ ግንባታ አልተደረገለትም” ብለዋል። እሳቸው ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ ግን በአምስት ዓመት ውስጥ የአየር ኃይሉን “የ 85 ዓመታት የቴክኖሎጂ፣የሰው ኃይል፣ ከአየር ጥቃት ኢትዮጵያን ለመከላከል በርከት ያሉ ቴክኖሎጂዎች ለመታጠቅ እና ብቃታችንን ከፍ ለማድረግ ሰርተናል” ብለዋል።

ዐቢይ አክለውም በሚቀጥሉት 5 ዓመታት የአየር ኃይሉን አቅም በእጥፍ ለማሳደግ መንግሥት ዕድቅ እና በጀት ለይቶ ከዋና ዋና አምራቾች ጋር ሥራ መጀመሩን ጠቁመዋል። ዛሬ ላይ ተቋሙ የአራተኛ ትውልድ የውጊያ ብቃት መገንባቱን ጠቅሰው በ 2030 ወደ አምስተኛው ትውልድ ይሻገራል ማለታቸውን ሰምተናል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ማብራሪያቸው “ጠላቶቻችን” ሲሉ ለጠሯቸው ሀገራት “የኢትዮጵያን ክብር፣የኢትዮጵያን አንድነት[እና] ብሔራዊ ትቅም ለማስከበር ተኝተን የማናድር መሆኑን በድጋሚ ማረጋገጥ እወዳለሁ፡ በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።

#Ethiopia #Eritrea
2 1 1.9K

Обсуждение 2

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram