avatar
EthioTube
@ethiotube
22.01.2026 09:15
በኢትዮጵያ ቀዳሚው ባለሐብት እንደሆኑ የሚነገርላቸው ሼህ መሐመድ ሁሴን ዓሊ አላሙዲ ዋቢ ሸበሌ ሆቴልን ገዙት

በቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ አስተዳደር በ40 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ተገንብቶ አገልግሎት የጀመረውን የዋቢ ሸበሌ ሆቴል ለባለሀብቱ ሼህ መሐመድ ሁሴን ዓሊ አላሙዲ ገዝተውታል።

የግዢ ስምምነቱን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድና የዋቢ ሸበሌ ሆቴል አክሲዮን ማኅበር የቦርድ ፀሓፊ ልዑል በዕደማርያም መኮንን ተፈራርመዋል። የሆቴሉን አገልግሎት ዓለም በደረሰበት ደረጃ በማዘመን ለእንግዶች ምቹና ጥራቱን የጠበቀ የማረፊያ ቦታ ለማድረግ እንደሚሰራ አቶ ጀማል አሕመድ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ 32ኛውን የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ለማዘጋጀት መመረጧን ተከትሎ ሚድሮክ ለጉባዔው ተሳታፊዎች ከሚሰራቸው ሆቴሎች አንዱ የዋቢሸበሌ ሆቴል መሆኑ ተመላክቷል። በዚህ መሰረት 60 ዓመት ገደማ ዕድሜ ያለውን ሆቴል ዘመናዊና ቅንጡ በሆነ መልኩ የማሪዮት ደረጃን (autograph collection by Marriot ) ጠብቆ ይታደሳል ተብሏል።

የዋቤ ሸበሌ ሆቴል የቦርድ ፀሓፊ ልዑል በዕደማርያም መኮንን የሆቴሉን ታሪክ ጠብቆ በማዘመን ለትዉልድ ለማሻገር በመስማማቱ ለሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በአዲስ አበባ ሜክሲኮ አካባቢ የተገነባው የዋቢ ሸበሌ ሆቴል፤ በደርግ ዘመን በመንግሥት ከተወረሰ በኋላ በ2000ዎቹ መጀመሪያ ላይ ግን ለንጉሣዊ ቤተሰቡ ወራሾች ተመልሷል።

#Ethiopia #AddisAbaba #WabeShebelleHotel #AlAmoudi #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
1 2.2K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram