avatar
EthioTube
@ethiotube
21.01.2026 20:52
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአምስት ዓመት በኋላ የሚረከባቸውን ዘጠኝ አውሮፕላኖችን ግዢ ፈፀመ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአምስት ዓመት በኋላ የሚረከባቸውን ዘጠኝ ቦይንግ 787-9 ድሪምላይነር አውሮፕላኖች መግዛቱን አስታወቀ። አየር መንገዱ ከቦይንግ ኩባንያ የገዛቸው አውሮፕላኖች በአውሮፓውያኑ የዘመን አቆጣጠር በ 2031 እስከ 2033 ባሉት ጊዜያት ውስጥ እንደሚረከብ ዛሬ ይፋ ባደረገው መረጃ አስታውቋል።

አየር መንገዱ የ 9 አውሮፕላኖችን ግዥ መፈፀሙ፤ የበረራ አድማሱን ለማስፋት፣ ዓለም አቀፍ ግንኙነቱን ለማሳድግ እንዲሁም የደንበኞቹን ፍላጎት ለሟሟላት እንደሚጠቅመው ገልጿል።

ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ መልኩ 11 አውሮፕላኖች ግዢ ተፈጽሞ ነበር። እነዚህ አውሮፕላኖች 737 ማክስ ጀት የተሰኙ ናቸው።በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአጠቃላይ የ 20 አውሮፕላኖችን ግዢ ፈጽሞ ለመረከብ በመጠበቅ ላይ ነው መባሉን ተመልክተናል።

#Ethiopia #EthiopianAirlines #Boeing #787dreamliner #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
1.9K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram