avatar
EthioTube
@ethiotube
18.01.2026 23:31
በከተራ በዓል ወቅት አራት አገልጋይ ወጣቶች በኤሌክትሪክ አደጋ ሕይወታቸው ማለፉ ተሰማ

በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በኮዬፈጬ ክፍለ ከተማ ዛሬ በተከበረው የከተራ በዓል፤ በፋንታ መድኃኔዓለም ደብር አገልጋይ የሆኑት አራት ወጣቶች በኤሌክትሪክ አደጋ ምክንያት ሕይወታቸው ማለፉን ቤተክርስቲያኗ ገልፃለች።

የአገልጋዮቹ ሕይወት ያለፈው ታቦቱን ለማጀብ የተጠቀሙት ሰረገላ ከመብራት ማስተላለፊያ ገመድ ጋር ተያይዞ መሆኑ ተሰምቷል። የመንበረ ፓትርያሪኩ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅና የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ከተማ አኀጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አባ ሳዊሮስ ይህን አሳዛኝ ክስተት አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በአደጋው የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጸው፤ “ልዑል እግዚአብሔር ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እንዲሰጥልንና ነፍሳቸውንም ከአብርሃ ፣ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጎን እንዲያኖርልን የዘወትር ጸሎታችን መሆኑን እንገልጻለን” ብለዋል።

#Ethiopia #AddisAbaba #Ketera #Timket #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
1 2.5K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram