avatar
EthioTube
@ethiotube
17.01.2026 21:37
በዋግ ኽምራ ዞን በስሕተት ተፈፅሟል በተባለ  የድሮን ጥቃት ካምፕ ውስጥ የነበሩ ቢያንስ 36 ሚሊሻዎች ተገደሉ

በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ስብሰባ ላይ በነበሩ የሚሊሻ አባላት ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ቢያንስ 36 ሰዎች መገደላቸውን አንድ የሰሃላ ሰየምት ወረዳ አመራር፣ የጤና ባለሙያ እና ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ።

በጥቃቱ 16 ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው እንዲሁም ካምፑ እና በውስጡ የነበሩ የጦር መሳሪያዎች እንደወደመ የወረዳ አመራሩ አስታውቀዋል።

በአካባቢው የሚገኙ የመከላከያ ሠራዊት አዛዦች ጥቃቱ የተፈጸመው "በስህተት" እንደሆነ መናገራቸውን የወረዳ አመራሩ እና ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ሐሙስ ጥር 7/2018 ዓ.ም. ጠዋት ላይ የድሮን ጥቃት የተፈጸመው በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር፤ ሰሃላ ሰየምት ወረዳ በሚገኝ የሚሊሻዎች ካምፕ ላይ እንደሆነ ዘገባው አመላክቷል።

ካምፑ የትጥቅ ማከማቻ እንዲሁም የፀጥታ ኃይሎች ማረፊያ እና መመገቢያ እንደሆነም ተገልጿል። ነዋሪዎች እንደሚናገሩት፤ ካምፑን ማዕከላቸው ያደረጉት የሚሊሻ አባላት በአካባቢው የሚንቀሳቀሱት የፋኖ ኃይሎች "ወደ ወረዳው እንዳይገቡ ጥበቃ" የሚያደርጉ ነበሩ።

ጥቃቱ በተፈጸመበት ሰዓት የሚሊሻ አባላቱ ከካምፑ ፊት ለፊት ከሚገኝ ሜዳ ላይ በአዛዣቸው "ስምሪት እየተሰጣቸው እና ቁርስ እየተመገቡ" እንደነበር የወረዳ አመራሩ ገልጸዋል። ሦስት የወረዳው ነዋሪዎችም ሚሊሻዎቹ ቁርስ እና ስብሰባ ላይ እንደነበሩ አረጋግጠዋል።

በአካባቢው የድሮኑ መታየት በሚሊሻዎች ዘንድ ስጋት ፈጥሮ የነበረ ቢሆንም "በወገን ላይ ጥቃት አይፈጽምም" የሚል መተማመን እንደነበረ ነዋሪዎቹ አስረድተዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የወረዳው አመራርም ተመሳሳይ ሀሳብ አንስተዋል።

#Ethiopia #Amhara
1 1 1.9K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram