avatar
EthioTube
@ethiotube
16.01.2026 21:40
ተወዳጁ የኪነጥበብ ባለሞያ ነጻነት ወርቅነህ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል

በቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢነት፣ በተዋናይነት፣ በማስታወቂያ ሥራ እና በሌሎች የጥበብ ሥራዎቹ ተወዳጅ ከሆኑ የጥበብ ሰዎች አንዱ የሆነው ነፃነት ወርቅነህ ዛሬ ታህሳስ 8/2017 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም ተለይቷል፡፡

ባደረበት ሕመም በድንገት ሕይወቱ ማለፉ የተሰማው ነፃነት፤ ለበርካታ ዓመታት በኢቢኤስ ቴሌቪዥን የሚተላለፈውን የቤተሰብ ጨዋታ ፕሮግራም በማዘጋጀት እና በማቅረብ ይታወቃል።

የአርቲስቱን ሕልፈት ተከትሎ ጠቅላይሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሀዘናቸውን ገልጸዋል። ዐቢይ በማኀበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ በድንገት በማረፉ ኀዘን ተሰምቶኛል ብለዋል።

ሕዳሴ ግድብ በተዘጋጀው የ2016 አዲስ ዓመት የመቀበያ ፕሮግራም የነበረውን አስተዋጽዖ ሁሌም እንደሚያስታውስቱት ገልጸው፤ ሁላችንም አዲሱን ዓመት በደስታ እንድንቀበል አድርጎን ነበር ሲሉ ሀዘናቸውን ገልጸዋል። በተመሳሳይ መልኩ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤም በነፃነት ሕልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።

አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ባለትዳርና የ3 ልጆች አባት ነበር። ኢትዮቲዩብ ለቤተሰቦቹ፣ እንዲሁም አድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛል።

#Ethiopia #NetsanetWorkneh #EBS #YebetesebChewata #EthiopianComedian #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
1.9K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram