avatar
EthioTube
@ethiotube
14.01.2026 00:52
በፌደራል ደረጃ ፈቃድ ከወሰዱ 585 ሺህ የንግድ ድርጅቶች ውስጥ 470 ሺህ የሚሆኑት የንግድ ፈቃዳቸው መሰረዙ ተገለፀ

በተጠናቀቀው የአውሮፓውያኑ 2024 በፌደራል ደረጃ ፈቃድ ከወሰዱ 585,000 የንግድ ድርጅቶች ውስጥ 470,000 የሚሆኑት የንግድ ፈቃዳቸው መሰረዙ ተገለፀ። ተሰርዘዋል አሊያም ሥራቸውን አቋርጠዋል የተባሉት የንግድ ተቋማት የክልሎችን የማያካትት ነው ሲል ሪፖርተር ዘግቧል።

የንግድ ተቋማቱ ከሥራ ውጭ እንዲሆኑ እና ፈቃዳቸው እንዲሰረዝ ምክንያት ሆነዋል ከተባሉ ተግዳሮቶች ውስጥ፤ በፈቃድ አሰጣጥ ላይ የሚደረጉ የሕግ ለውጦች፣ ማክሮኢኮኖሚው ላይ ያሉ ችግሮች፣ ተቋማቱ በቀላሉ ብድር ማግኘት አለመቻላቸው እንደሆነ ተገልጿል።

ተዘግተዋል አሊያም የንግድ ፈቃዳቸው ተሰርዟል ከተባሉ ውስጥ 360,000 የሚሆኑት ጥቃቅን ቢዝነሶች ሲሆኑ 90,000 የሚሆኑት ደግሞ አነስተኛ ተብለው የሚመደቡ ናቸው። ከ 23,000 በላይ የሚሆኑት መካከለኛ ቢዝነሶች መሆናቸው በዘገባው ላይ ተጠቅሷል። ከፍተኛ ኢንተርፕራይዝ ተብለው በሚመደቡ የቢዝነስ ዓይነቶች ውስጥም 86 በመቶ የሚሆኑት ሥራቸውን እንዳቋረጡ ተገልጿል።

ንግድ እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ በሎጀስቲክስ እና ትራንስፖርት ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶች፣ በአይሲቲ እንዲሁም በኮንስትራክሽን ላይ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በርካታ ድርጅቶች ከገበያ ወጥተዋል። በተጠናቀቀው 2024 13,500 የሚሆኑ በግብርና ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ተቋማት በተመሳሳይ መልኩ ሥራቸውን መቀጠል ባለመቻላቸው የንግድ ፈቃዳቸው ተሰርዟል።

የንግድ ፈቃዳቸው ተሰርዞ ሥራቸውን ያቋረጡ 470,000 የንግድ እና አገልግሎት ተቋማት በሥራ ፈጠራ ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋት ደቅኗል መባሉን ከዘገባው ላይ ተመልክተናል።

#Ethiopia #AddisAbaba
1 2.1K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram