avatar
EthioTube
@ethiotube
09.01.2026 23:23
"በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በተጠርጣሪዎች ቁጥር መብዛት ምክንያት ከፍተኛ መጨናነቅ ተፈጥሯል" ኢሰመኮ

የቂሊንጦ የጊዜ ቀጠሮ ማረፊያ ማእከል መያዝ ከሚችለው በላይ ተጠርጣሪዎች ያያዘ በመሆኑ ከፍተኛ መጨናነቅ እንደተፈጠረ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ይህን ያስታወቀው የተቋሙ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በማዕከሉ ያደረጉትን ጉብኝት አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ነው።

በማረሚያ ቤቱ “ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ተጠርጣሪዎች”፣ ከሌሎች ተለይተው አለመያዛቸው፣መዝጊያ የሌላቸው መጸዳጃ እና መታጠቢያ ቤቶችን ጨምሮ የተወሰኑ የውኃ ቧንቧዎች አገልግሎት ያቆሙ መሆናቸው ኢሰመኮ ትኩረት የሚሽ ጉዳዮች በማለት ገልጿቸዋል።

ከነዚህ በተጨማሪ በማረሚያ ቤቱ የተወሰኑ ዞኖች ለተጠርጣሪዎች በቂ የመንቀሳቀሻ ቦታ አለመኖሩ፣ ተጠርጣሪዎች ለመያዝ የሚፈቀድላቸው አነስተኛ የብር መጠን (እስከ 200 ብር ብቻ) መሆኑ የሚያስፈልጓቸውን ሸቀጦች ለመግዛት አለመቻላቸው ሌላው ክፍተት ነው ተብሏል።

ተጠርጣሪዎች የሚፈልጓቸውን መጻሕፍት ለማስገባት መቸገራቸው እንዲሁም ለአንድ ተጠርጣሪ የእለት ቀለብ የተመደበው 35 ብር ምግብ ለማቅረብ በቂ አለመሆኑ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች መሆናቸው ኢሰመኮ በጉብኝቱ ለመገንዘብ ችሏል፡፡

በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የተፈጠረውን መጨናነቅን ለማስቀረት ፍርድ የተሰጣቸውን ሰዎች ወደ ቃሊቲ ከፍተኛ ማረሚያ ተቋም ለማዛወር በማረሚያ ቤቱ እንደተወሰነ ተገልጿል።

ይህ መፍትሔ በፍጥነት ተግባራዊ እንዲደረግ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ አሳስበዋል።

#Ethiopia #EthiopianPrison #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
2 2 2.4K

Обсуждение 2

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram