avatar
EthioTube
@ethiotube
09.01.2026 22:27
በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ያለው ውጥረት ወደ ጦርነት ካመራ “ቀጠናው ወደለየለት ቀውስ ይገባል” ሲል ኢንተርናሽናል ክራይሲስ ግሩፕ አስጠነቀቀ

በእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ካለችው ሱዳን በተጨማሪ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ያለው ውጥረት ወደ ጦርነት ካመራ የምሥራቅ አፍሪካ ቀጠና “ወደለየለት ቀውስ ይገባል” ሲል ኢንተርናሽናል ክራይሲስ ግሩፕ አጠንቅቋል።

ተቋሙ ይህን የገለጸው በአውሮፓውያኑ 2026 ሊከሰቱ የሚችሉ እና የሚቀጥሉ ሲል 10 ጦርነቶችን ይፋ ባደረገበት ሪፖርት ላይ ነው። በዚሁ ሪፖርት ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ለወራት ያህል እርስ በእርስ ሲወቃቀሱ እና ሲካሰሱ መቆየታቸውን አስታውሷል። ይሁን እንጂ ዓለም አቀፉ ማኀበረሰብ በሀገራቱ መካከል “እየተጠመቀ ያለውን ቀውስ ችላ ብሎታል” ሲል ገልጿል።

ኤርትራ መንግሥት፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ውግያ የሚያደርጉ ታጣቂዎችን “እያሰለጠነ” እና የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን “እያስታጠቀ ነው” የሚል ክስ እንደሚቀርብበት ሪፖርቱ ያትታል። በተመሳሳይ መልኩ የኤርትራ መንግሥት ደግሞ ኢትዮጵያን “በጸብ አጫሪነት” እየወቀሰ መሆኑን አመላክቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ በሁለቱ ሀገራት መካከል የነበረው ግንኙነት ተሻሽሎ እንደነበር የሚያትተው ሪፖርቱ፤ በፌደራል መንግሥት እና በህወሓት መካከል ጦርነት ሲካሔድ የኤርትራ ወታደሮችም ተሳትፈው እንደነበር አስታውሷል። ሆኖም የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ከተፈረመ በኋላ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ወዳጅነት ወደ ቅራኔ መለወጡን ኢንተርናሽናል ክራይሲስ ግሩፕ ገልጿል።

ኢትዮጵያ የባሕር በር እና የወደብ ፍላጎት ይፋ ማድረጓን ተከትሎ ደግሞ አስመራ “ልወረር እችላለሁ” በሚል ስጋት ውስጥ ናት መባሉን ከሪፖርቱ ላይ ተመልክተናል።

#Ethiopia #Eritrea
1 1 2K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram